አቤ ቶክቻው ተሰደደ

ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለዛ ባለው አዝኛኝ ጽሁፉ ፖለቲካውን እያዋዛ የህብረተሰቡን ብሶት ሲያሰማ የቆየው “አቤ ቶክቻው” አገር ለቅቆ ወጣ።

አቤ ቶክቻው ቀደም ሲል ባውራምባ ታይምስ፤አሁን ደግሞ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረቡ በተደጋጋሚ ከደህንነት ሀይሎች  ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው ቆይቷል።

በተለይ ባለፈው ሳምንት፦” ጠቅላይ ሚኒስትሬ እንደሚያነቡኝ ባወቅኩ ጊዜ ደስ አለኝ”በሚል ርዕስ አቶ መለስ የዘንድሮውን ፓርላማ የ ስራ ዘመን ሲከፍቱ ስላደረጓቸው ንግግሮች  ያቀረበውን ተችት ተከትሎ ከፍ ያለ ዛቻ ሲሰነዘርበትና ክትትል ሲደረግበት መሰንበቱ ታውቋል።

የአቤ ቶክቾውን መሰደድ አስመልክቶ አንድ የስራ ባልደረባው  ” ስደት ሲበዛ ጥሩ ባይሆንም፣ እንግዲህ ምን ይደረግ ያለንበት እውነታ ይኸው ነው” ብሎአል።