የገናን በአል ምክንያት በማድረግ የእርድ እንስሳት ዋጋ ጨመረ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው የገናን በአል ተከትሎ የእርድ እንስሳት ዋጋና  በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የእርድ ከብት ከ12 ሺ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዶሮ ከ170 እስከ 200 ብር፣ በግ ከ1200 ብር እስከ 1700 ብር፣ ፍየል ከ1000 እስከ 1800 ብር በመሸት ላይ ነው። ቅቤ  በኪሎ በአማካኝ 130 ብር ዘይት 24 ብር ...

Read More »

ዶክተር መረራ ጉዲና በድጋሚ ድርጅታቸው ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ (ኦህኮ) ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላይ ጉባኤ፤ ፓርቲውን ላለፉት 16 ዓመታት ሲመሩ የቆዩትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጧል ። በ1997 ዓ.ም ከቀድሞ ቅንጅት በመቀጠል በፓርላማው ከፍተኛ ድምፅ አግኝቶ የነበረው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረትም (ኢዴኃህ)፤ እንዲፈርስ ተወስኗል። “እርስዎ በድጋሚ የተመረጡት ፓርቲው ሌላ ሰው ስለሌለው ነው ወይ?” ተብለው  የተጠየቁት ...

Read More »

በ3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል አካባቢ የሚገኘው የአወሊያ ቁጥር 2 ት/ት ቤት ተማሪዎች በትላንትናው ቀን ማክሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በ3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል አካባቢ የሚገኘው የአወሊያ ቁጥር 2 ት/ት ቤት ተማሪዎች በትላንትናው ቀን ማክሰኞ በ እስላማዊ ምክር ቤት ወይም መጅሊስ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ፡፡ ተማሪዎቹ ቀኑን ሙሉ የዋለ ተቃውሞ ሊያሰሙ የቻሉበት ምክንያት፤ መጅሊሱ የአረብኛ መምህሮችን ከትምህርት ቤቱ በማባረሩና፤ በምትኩ በራሳቸው ያሰለጠኗቸውንና የአሕባህሽ ተከታይ የሆኑትን በማሰማራት ተማሪዎቹን ከእስልምና ለማስወጣት በማሰባቸው ነው። ተማሪዋቹ የአህባሽን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በመንግስት ላይ ድል ተቀዳጀሁ አለ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የዘመቻ ደምመላሽ ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ዶጋው ልዩ ስሙ ጉርማጭት በተባለ አካባቢ ላይ በታህሳስ 21- 2004 ዓ.ም በመቶ አለቃ ገበየሁ ከሚመራው ልዩ ሃይል ጋር በተካሄደ ውጊያ 9 የመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂዎች መግደሉን፣  16ት ወታደሮችን ደግሞ ማቁሰሉን ገልጧል። ከባድና ቀላል መሳሪያዎችን ከነ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን ያስታወቀው  የኢሕአግ ወታደራዊ መምሪያ ፣ የዘመቻ ደምመላሽ ...

Read More »

ሶማሊ-ላንድ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የተመዘገቡ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስገድዳ ወደ ኢትዮጵያ መለሰች

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ሶማሊ-ላንድ  በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የተመዘገቡ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን  አስገድዳ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጓን ሂዩማን ራይትስ ዎች ገለጠ። ዳግም የዚህ ዓይነት ድርጊት እንዳትፈጽምም ጠይቋል። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር  ባለፈው ዲሴምበር 28፤  የሶማሊላንድ አስተዳደር  ለመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ወደ ሶስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ እንዲሰጣቸው አመልክተው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉትን 20 ኢትዮጵያውያን በሀይል በማስገደድ ወደ ...

Read More »

በወጣቶች አነሳሽነት የተቋቋመው ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ መሥራች ጉባዔውን ባለፈው እሑድ አካሄዷ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲውን ከመሠረቱት ግለሰቦች መካከል መርህ ይክበር በሚል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት ይገኙበታል፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ቃል አቀባይ አቶ አርዓያ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እሑድ በፓርቲው ጽሕፈት ቤት በተካሄደው መሥራች ጉባዔ 150 ሰዎች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ይልቃል ጌታሁን  የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ሰላሳ ሰባት አባላት ያሉት የፓርቲው ...

Read More »

“ ከአሁን በሁዋላ የኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ ተለይቶ የሚታይ አይደለም” ሲሉ አቶ አሚን ጁንዲ ገለጹ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ አሚን ይህን ያሉት፤ የድርጅታቸውን አዲስ የፕሮግራም ለውጥ አስመልክቶ ከህብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አዲሱ አቋማችሁ በአቶ መለስ ስርዓት ላይ ከሚፈጥረው ጫና አኳያ እንዲሁም እየለወጣችሁት ያላችሁት ለረዥም ጊዜ ስታራምዱት የቆያችሁትን አቋም ከመሆኑ አንፃር ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ቢነሳባችሁ ምን ያህል ተዘጋጅታችሁዋል? በማለትም የራዲዮው ...

Read More »

በዋሽንግተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሻማ መብራት ስነስርአት አካሄዱ

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በ”ማርች ፎር ፍሪደም”ና በሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስተባባሪነት በየወሩ በአሜሪካን ፕሬዚዳንት መኖሪያ ፊት ለፊት የሚካሄደውና በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የሚያስበው የሻማ ማብራት ስነስርአት በሞቀ ሁኔታ ተካሂዷል።  እስክንደር ነጋ እና አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ሌሎች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች  ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለሶስተኛ ግዜ በተካሄደው የሻማ ማብራት ስነስርአት ላይ አያሌ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ...

Read More »

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያን አቶ በረከት ስምኦን ወደ ሱዳን መጥተው ከተመለሱ በሁዋላ፣ የሚደርስብን እንግልት ጨምሮአል ይላሉ

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ስደተኞች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን እየተጠየቁ በመንገላታት ላይ ናቸው። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ፓስፖርት ከሌለው ስራ መስራት አይችልም የሚል መመሪያ መውጣቱን ስደተኞች ይናገራሉ። አላማው በሱዳን  የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረገው ስምምነት መሆኑን ስደተኞች ይናገራሉ። በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የሚደርስባቸውን በደል በተመለከተ በተደጋጋሚ አቤቱታ እንደሚያሰሙ ቢታወቅም፣ ...

Read More »

ሶማሊያ የገባው የኢትዮጵያ ጦር ከአልሸባብ ጋር የሚያደርገው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

  ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በለደወይን የምትባለውን የሶማሊያን  ግዛት ከአልሸባብ እጅ መልሶ የነጠቀው የኢትዮጵያ ጦር በሚቀጥሉት ቀናት ከአልሸባብ ተዋጊዎች ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ሲሉ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው። ወል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው አልሸባብ በበለደወይን አጎራባች ስፍራዎች  ላይ የነበሩትን ተጠባባቂ ወታደሮቹን ወደ ከተማዋ በማስጠጋት ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት እያደረገ ነው። በሌለ በኩል የኬንያ ጦር የአልሸባብን የኢኮኖሚ ምንጭ ...

Read More »