በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያን አቶ በረከት ስምኦን ወደ ሱዳን መጥተው ከተመለሱ በሁዋላ፣ የሚደርስብን እንግልት ጨምሮአል ይላሉ

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-ስደተኞች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን እየተጠየቁ በመንገላታት ላይ ናቸው።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ፓስፖርት ከሌለው ስራ መስራት አይችልም የሚል መመሪያ መውጣቱን ስደተኞች ይናገራሉ።

አላማው በሱዳን  የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረገው ስምምነት መሆኑን ስደተኞች ይናገራሉ።

በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች የሚደርስባቸውን በደል በተመለከተ በተደጋጋሚ አቤቱታ እንደሚያሰሙ ቢታወቅም፣ እስከሁን ግን ይህ ነው የሚባል በቂ መላሽ ሲያገኙ አይታይም።