ታህሳስ 28 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:- “መሬትን ለ አራሹ ለምን አላከፋፈልክም ብለን የሀይለሥላሴን ስርዓት እንደማንጠይቅ ሁሉ፤ ዲሞክራሲንም ‘ልማታዊ መንግስት ነኝ’እያለ ከሚቀልደው ኢህአዴግ መጠበቅ የለብንም”ሲሉ ታዋቂው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ተናገሩ። ዶክተር ዳኛቸው ይህን ያሉት፤ ሰሞኑን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ጽህፈት ቤት ውስጥ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነው። በመኢአድ የውይይት መድረክ ላይ ተጋባዥ ተናጋሪ ...
Read More »የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተወካይ መርካቶ ውጥንቅጡ እንደወጣና በአስፈሪ ጎዳና ላይ መገኘቱንና ተናገሩ
ታህሳስ 28 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተወካይ መርካቶ ውጥንቅጡ እንደወጣና በአስፈሪ ጎዳና ላይ መገኘቱንና ፣ ‹‹ነጋዴው ታግሶና ቆሞ ያለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው›› መሆኑን ተናገሩ ተወካዩ ይህን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ.ም የንግድ ምክር ቤት የሥራ አመራርና አባላትን፣ እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች ተወካዮችን በአስተዳደሩ የባህል አዳራሽ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ ባወያየበት ...
Read More »የመለስ አገዛዝ በዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለው ዘግናኝ ድርጊት ተባብሶ ቀጥሏል
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል አንዲት የመኢአድ አባል በ 28 ጥይት ተደብድባ ስትገደል፤ በሰሜን ጎንደር በበለሳ ወረዳ አንድ የመኢአድ ስራ አስፈፃሚ- አናቱን በመጥረቢያ ተመትቶአል። የአንድነት ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፤በደቡብ ክልላዊ በደራሼ ልዩ ወረዳ በሠገን የምርጫ ክልል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን /መኢአድን/ በመወከል በምርጫ 2002 ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተወዳደረችው ወ/ሮ አማረች ገለኔ በአገዛዙ ታጣቂዎች በ28 ጥይት ተደብድባ ...
Read More »ሀዲያ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት ሁለት ፖሊሶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምሩቃን ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለፀ
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ሀዲያ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በዞኑ መስተዳድር መካከል የተፈጠረን አለመግባባት ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት ሁለት ፖሊሶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምሩቃን ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። እንደ ፍኖተ-ነፃነት ዘገባ ግጭቱ ሊፈጠር የቻለው በሀዲያ ዞን ሆሣዕና ከተማ የሚገኙ በተለያየ ዓመት ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ሥራ ያጡ ወጣቶች ለዞኑ መስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው ታስረው በመደብደባቸው ነው። ምንጮቹን በመጥቀስ ጋዜጣው እንደዘገበው፤ከተለያዩ ...
Read More »በአማራ ክልል በመንግስትና በመምህራን መካከል ያለው ፍጥጫ አሁንም እንደቀጠለ ነው
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የክልሉን መምህራን ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ መንግስቱ አህመዴን ከስልጣን ለማውረድ በተጀመረው እንቅስቃሴ መምህራን እልህ ውስጥ መግባታቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህራን ተነግረዋል። ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት የመምህራን ማህበር መምህራንን በተደጋጋሚ ስብሰባ በመጥራት አዳዲስ አመራሮችን እንደሚርጡ ለማግባባት ሙከራ ቢያደርግም፣ መምህራን ግን አሁንም በማህበራቸው መሪ ጽኑ እምነት እንዳላቸው በመጥቀስ የመንግስትን ማግባባትና ጫና አልተቀበሉትም። በሰሜን ጎንደር፣ በምእራብ ጎጃምና ...
Read More »በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈጠረው የጎሳ ግጭት ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎችንም እያተራመሰ ነው ተባለ
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈጠረው የጎሳ ግጭት ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎችንም እያተራመሰ ነው ተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ በቦረናና በገርባ ጎሳዎች መካከል ከግጦሽ መሬትና ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ወደ ኬንያም ተስፋፋቶ በአካባቢው የሚገኙ 17 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ታወቋል። ከአካባቢው ርቀት አንጻር እስካሁን ድረስ የተጠናከረ መረጃ ባይቀርብም፣ በሞያሌ አካባቢ ...
Read More »በፈረንሳይ ቴልኮም ላለፉት ሁለት አመታት ሲተዳደር የነበረው ቴሌ ፣ የተሻለ ለውጥ ማምጣት እንዳልቻለ ሰራተኞች ተናገሩ
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድርጅቱ ሰራተኞች እንደገለጡት 34 የሚሆኑ የፈረንሳይ የቴልኮም ኩባንያ ሰራተኞች የቴሌን ማኔጅመንት ለማሻሻል የ30 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 600 ሚሊዮን ብር በላይ ኮንትራት ቢፋራረሙም በድርጅቱ ላይ ከውድቀት በስተቀር እድገት አልመጣም። በሁሉም ዘርፎች ያለው አግልግሎት ተዳክሟል የሚሉት ሰራተኞች፣ የቀድሞውን ማኔጅመንት የተካው ከመከላከያ ሚኒስቴር የተውጣጡት የህወሀት የጦር መኮንኖችም ምንም ለውጥ ሊያመጡ አልቻሉም ይላሉ። በቴሌ ...
Read More »ባይዶዋን የተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከተማዋን ለአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል አስረክቦ ሊወጣ ነው ተባለ
ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ግዛት ለቆ እንዲወጣ የተወሰነው የአፍሪካ ህበረት የሰላምና የደህንነት ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ፣ የኬንያ ፣ የዩጋንዳ እና የብሩንዲ ጥምር ጦር ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውን አልሸባብን ለመውጋት በእየአቅጣጫው ዘመቻዎችን መክፈታቸው ይታወሳል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱዌሊ ሙሀመድ በበለደወይን መገኘታቸውን ቢቢሲ አክሎ ዘግቧል። የኢትዮጵያን ጦር 5 ሲ የሚሆኑት ...
Read More »ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ
ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ የጸረ ሽብር የመረጃ መእከል ለግልና ለመንግስት ባንኮች ባወረደው መመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከ200 ሺ ብር ጀምሮ በባንኮች ለማስቀመጥ ወይም ለማውጣት በሚሄድበት ጊዜ፣ ባንኮች የግለሰቦችን ስምና ማንነት ለብሄራዊ ...
Read More »ኢቲቪ ‘‘አኬልዳማ’’ በሚል ርዕስ ያስተላለፈው ፕሮፓጋንዳ የተሰራው መንግስት እልክ በመጋባቱ መሆኑን አቶ በረከት ስምኦን ጠቆሙ
ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ‘‘አኬልዳማ’’ በሚል ርዕስ ያስተላለፈው ፕሮፓጋንዳ እንዲሰራ የተወሰነው፤ መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከፕሬሶች ጋር እልክ በመጋባቱ መሆኑን አቶ በረከት ስምኦን ጠቆሙ። አብዛኛው ህዝብ-ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓመታዊ ግብር አልከፍልም ማለቱንም ተናገሩ። ለዝርዝሩ ደረጀ ሀብተወልድ፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስምኦን ሰሞኑን ለሕዝብ ...
Read More »