መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋሙ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ናዮኪ ሺኖሀራ ከአቶ መለስ እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ ፣ ኢትዮጵያ የገንዘብ ግሽበትን በመቆጣጠር፣ እየጨመረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት በማስታገስና ኢንቨስትመንትን በመሳብ በኩል ከፍተኛ ፈተናዎች ተደቅነውባታል። ምክትል ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት አመቺ የሆኑ ለውጦችን እንዲያካሂድና በቂ የሆነ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲኖር መስራት እንዳለበት ...
Read More »የአልሸባብ ሚሊሻዎች በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ሀሰት ነው አለ
መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአልሸባብ ሚሊሻዎች ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ላይ በከፈቱት ጥቃት ከፍ ያለ ጉዳት እንዳደረሱ በዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን የተሰራጨውን ዜና ውሸት ነው ስትል ኢትዮጵያ አስተባበለች። አልሸባብ በበኩሉ የማረካቸውን የኢትዮጵያ ወታደሮች የድምፅ መረጃ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ በማስታወቅ፤ ኢትዮጵያ የደረሰባትን ኪሳራ ልታስተባብል እንደማትችል ገልጿል። አልሸባብ ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ጦር ላይ መንገድ ዘግቶ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ፤ በርካታ ...
Read More »ከሰባ በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንዳለው አልሸባብ፤ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ላይ ድንገት በከፈተው የማጥቃት እርምጃ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ከአካባቢው የሚወጡ ሪፖርቶች ያመላክታሉ። እንደ ዜና አውታሩ ዘገባ፤የኢትዮጵያና ጥቂት የሶማሊያ ወታደሮች የማዕከላዊ ጌዲኦ አካል በሆነችው በዩኩሩት ባለፈው ማክሰኞ ንጋት ላይ በአልሸባብ ተዋጊዎች ተከበቡ። ከዚያም ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ውጊያ ተካሄደ። በሞቃዲሾ ሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ...
Read More »ሙስሊሞች የኮሚቴውን ውሳኔ ካደመጡ በሁዋላ አለመረጋጋት እየታየ ነው
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጁማ ጸሎት በአወልያ ከ400 ሺ ህዝብ ያላነሱ ሙስሊሞች ተገኝተው የኮሚቴውን ውሳኔ ካደመጡ በሁዋላ አለመረጋጋት እየታየ መሆኑ ተገለጠ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተለው ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው እለት ሙስሊሙ የመረጣቸው ኮሚቴዎች እንደታሰሩ የሚያመለክቱ፣ ሙስሊሙ ተቃውሞውን እንዲያሰማ የሚጠይቁ መልእክቶች በሞባይል ስልክ ( ኤስ ኤም ኤስ) እና በበራሪ ወረቀቶች ሳይቀር ሲበተን አርፍዷል። ይሁን እንጅ ህዝበ ሙስሊሙ አመራሮቹ ያልታሰሩ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን አባረረ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት 5 ቀናት በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ግምገማ የመስተዳድሩ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሐይሌ ፍሰሐ፣ ምክትላቸው አቶ አበበ ዘልኡል፣ የመሬት አስተዳደር እና ግንባታ ሃለፊ ቃሲም ፈንቴእና ምክትላቸው ይርጋለም አለሙ፣ የከተማ ውሀና የመሬት ልማት ባንክ ሃላፊ አቶ ሳህለ ሰርሻ፣ የአዲስ አበባ የዲዛይንና ግንባታ ልማት ሃለፊ አቶ አበበ ከበደ ጃለታ ከስራ እንዲባረሩ ተደርጓል። ባለስልጣኖቹ የተባረሩት ...
Read More »ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በጠና ታመዋል
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በጠና ታመው ኮሪያ ሆስፒታል መግባታቸውን አዲስ አድማስ ዘገበ። ላለፉት 11 ዓመታት በኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄርነት የቆዩት መቶ አለቃ ግርማ፤ የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሥልጣን ለመውረድ የስድስት ወራት ዕድሜ ቀርቷቸዋል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን በመሰናበቻቸው ዋዜማ በጠና ታመው በኮሪያ ሆስፒታል የቅርብ እርዳታና ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የሆስፒታሉ ምንጮች ለጋዜጣው እንደጠቆሙት፤ ፕሬዚዳንቱ ከትናንት በስቲያ በጠና ታመው ...
Read More »በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኖርዌይ መንግስት በስደተኞች ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኖርሜይ መንግስት በስደተኞች ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ በስዊዲን የኖርዌይ ኢምባሲ ፊት ለፊት ኢትዮጵያውያውያኑ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የኖርዌይ መንግስት የወሰደው እርምጃ ህገወጥ ነው ብለዋል። በተቃውሞው ሰልፍ ላይ በስቶክሆልም ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ደጋፊ የውጭ አገር ዜጎች ተገኝተዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...
Read More »በአረብ አገራት በሚኖሩኢትዮጵያውያን ግፍ እየተፈፀመባቸው ነው
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በአረብ አገራት በሚኖሩ ሴት ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍ ህሊና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ መምጣቱ በሚነገርበት ወቅት የሊባኖስ መንግስት ግፍ በሚፈጽሙት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ በኢትዮጵያዊቱ የቤት ሰራተኛ ላይ በአደባባይ የተወሰደውን እርምጃ አውግዞ፣ ጉዳዩ ተጣርቶ እርምጃ እንደሚወሰድ የማስታወቂያ ሚኒሰትሩ ተናግረዋል። የሊባኖስ መንግስት ድርጊቱን ያወገዘው ኤል ቢሲ የተባለ የሊባኖስ ቴሌቪዥን አንድ ሊባኖሳዊ ...
Read More »ጆሴፍ ኮኒን ለማደን የተሰራጨው ፊልም ኢንተርኔትን አጨናነቀ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የህፃናት ቀበኛ የሆነውን ጆሴፍ ኮኒን ለማደን የተሰራጨው ፊልም በአራት ቀናት ብቻ በ60 ሚሊዮን ጎብኝዎች በመታየት የኢንተርኔት መስመሮችን ማጨናነቁ ተዘገበ ። ሰሞኑን የተሰራጨው ይህ ፊልም እንደሚያስረዳው፤ የኡጋንዳው የጎሬላ ተዋጊና የ”ጌታ ተጋዳይ ሠራዊት” (ሎርድ’ስ ሬዚዝታንስ አርሚ) መሪ ጆሴፍ ኮኒ፤ በኡጋንዳ ከ 60 ሺህ በላይ ህፃናትን ጠልፏል። ኮኒን ለማደን በዩቲዩብ የተሰራጨውና በጥቂት ቀናት ወደ 60 ሚሊዮን ...
Read More »ሰመጉ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና መታሰራቸውን አስታወቀ
የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲፈጸሙ የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በማጋለጥ አለማቀፍ እውቅና ያተረፈው ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) ወይም አሁን ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ሰመጉ) እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ባወጣው 35ኛ መደበኛ ጉባኤ በአገሪቱ ውስጥ ባለፈው አንድ አመት የታየቱን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አውጥቷል። በሪፖርቱ መሰረት በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በቆንሴ አርኪ ገበሬ ...
Read More »