አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በርካታ ችግሮች ተደቅነውባታል አለ

መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋሙ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ናዮኪ ሺኖሀራ ከአቶ መለስ እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ ፣ ኢትዮጵያ የገንዘብ ግሽበትን በመቆጣጠር፣ እየጨመረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት በማስታገስና ኢንቨስትመንትን በመሳብ በኩል ከፍተኛ ፈተናዎች ተደቅነውባታል።

ምክትል ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት አመቺ የሆኑ ለውጦችን እንዲያካሂድና በቂ የሆነ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲኖር መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን አይ ኤም ኤፍ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ውጤት ደስተኛ መሆኑን ቢዘግቡም ከመግለጫው ለመረዳት እንደሚቻለው፣ የገንዘብ ተቋሙ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ አለመርካቱን የሚያሳይ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide