የአዲስ አበባ መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን አባረረ

መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-ባለፉት 5 ቀናት በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው  ግምገማ የመስተዳድሩ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሐይሌ ፍሰሐ፣ ምክትላቸው አቶ አበበ ዘልኡል፣ የመሬት አስተዳደር እና ግንባታ ሃለፊ ቃሲም ፈንቴእና ምክትላቸው ይርጋለም አለሙ፣ የከተማ ውሀና የመሬት ልማት ባንክ ሃላፊ አቶ ሳህለ ሰርሻ፣ የአዲስ አበባ የዲዛይንና ግንባታ ልማት ሃለፊ አቶ አበበ ከበደ ጃለታ ከስራ እንዲባረሩ ተደርጓል።

ባለስልጣኖቹ የተባረሩት ከሙስ እና ከብቃት ጋር በተያያዘ መሆኑ ቢነገርም ፣ አመራሮቹ ከከንቲባው ኩማ ደመቅሳ ጋር ያላቸው ልዩነት መስፋት በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚታየው ችግር እየተበራከተ መምጣት የአቶ ኩማን የአመራር ብቃት ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።

የአፍሪካ መዲና በሆነቸው አዲስ አበባ አሁንም የወንዝ ውሀ የሚጠቀሙ በርካታ አካባቢዎች አሉ። ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ60 በመቶ በሚሆነው የአዲስ አበባ ክፍል ለአራት ቀናት ውሀ ተቋርጦ ነበር። በመሬት አስተዳዳር፣ በትራንስፖርት እጥረትና በተለያዩ  መስሪያቤቶች የሚታየው ሙስና አስተዳደሩ ብቃት የለሌው መሆኑ ታይቷል።

በዚህም የተነሳ ኢህአዴግ ማንኛው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አባሎቹ እና በመስተዳድሩ ውስጥ የሚሰሩ ደጋፊዎቹ  ትምህርታቸውን አቋርጠው በቅስቀሳ ላይ እንዲሰማሩ መመሪያ አውጥቷል። አቶ ኩማ ደመቅሳ አዲስ አበባን ማስተዳደር እየተሳናቸው በመምጣቱ እርምጃውን በበታች ሾሙች ላይ በመውሰድ ራሳቸውን ነጻ ማድረጋቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ። ይሁን እንጅ አሁን በከተማው የሚሰማው የህዝብ ምሬት እያየለ ከመጣ እርሳቸውም ቀዩ ካርድ ከሚመዘዝባቸው መካከል ይሆናሉ ሲሉ ታዛቢዎች ያክላሉ።

አቶ ኩማ የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ የኢህአዴግ አባል ሆነው መቀጠላቸው፣ ህወሀት ከሁለት ሲከፈል የእነ አቶ ስየ ደጋፊ ተደርገው በመቆጠራቸው ተባረው ከቆዩ በሁዋላ፣ እንደገና ምህርት ተደርጎላቸው ወደ ስልጣን ቦታ የተመለሱ ናቸው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide