በአረብ አገራት በሚኖሩኢትዮጵያውያን ግፍ እየተፈፀመባቸው ነው

መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-በአረብ አገራት በሚኖሩ ሴት ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍ ህሊና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ መምጣቱ በሚነገርበት ወቅት የሊባኖስ መንግስት ግፍ በሚፈጽሙት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ በኢትዮጵያዊቱ የቤት ሰራተኛ ላይ በአደባባይ የተወሰደውን እርምጃ አውግዞ፣ ጉዳዩ ተጣርቶ እርምጃ እንደሚወሰድ የማስታወቂያ ሚኒሰትሩ ተናግረዋል።

የሊባኖስ መንግስት ድርጊቱን ያወገዘው ኤል ቢሲ የተባለ የሊባኖስ ቴሌቪዥን አንድ ሊባኖሳዊ ኢትዮጵያዊቷን ወጣት በአደባባይ እየደበደበ በጉልበት ሊወስዳት ሲሞክር የሚያሳየውን ፊልም ይፋ ካደረገ በሁዋላ ነው።

ለህዝብ በተላለፈው የቪዲዮ ፊልም በአማርኛ ቋንቋ ስትማጸን ትሰማለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ በየመን ባልታወቁ ሰዎች ከታገቱ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል 128 ቱ መለቀቃቸውን ግሩም ተክለሀይማኖት ከየመን ዘግቧል።

ከተፈቱት ኢትዮጵያውያን መካከል የተወሰኑት ፊታቸው በእሳት ተቃጥሎአል፡፤ ህጻናትና አሮጊቶችም ይገኙበታል። በአሁኑ ገዚ ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያን በቡድን በተደራጁ ታጋቾች ባልታወቀ ቦታ ታግተው እንደሚገኙ ዘገባው ከዘገባው ለመረዳት ይቻላል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide