ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አንድነት ማህበር ሊቀመንበርና አጋሮቻቸው የማህበሩን ሃብትና ንብረት ያለአግባብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉትና እየመዘበሩት እንደሚገኙ፣ አንዳንድ የማህበሩ አባላት ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ። ቅዱስ ሃብት በላቸው ከአውስትራሊያ ባጠናቀረው ዜና መሰረት የማህበሩ ሊቀመንበር የሆኑት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ቁጥሩ ቀላል የማይባል ጥሬ ገንዘብና ንብረት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከዚህም መካከል በዓመት ...
Read More »በአቡነ ጳውሎስ አማካይነት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለቀናት እየታመሰ ነው
ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድረ-ገጹ የስብሰባ ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ችግሩ የተጀመረው ገና ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው ዝርዝር የመወያያ አጀንዳዎቹን ለምልአተ ጉባኤው ሲያቀርብ ነው። ኮሚቴው ካቀረባቸው 20 አጀንዳዎች ውስጥ ርእሰ-መንበሩ አቡነ ጳውሎስ በተራ ቁጥር 18 ላይ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙ አባቶች ጋራ የተጀመረው ዕርቅ ጉዳይ በአጀንዳነት መያዙን ይቃወማሉ። የ እርቁ ጉዳይ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትም፦ “ፖሊቲከኞች ናቸው” በሚልም በዕርቀ- ሰላሙ ሂደት ...
Read More »የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሩጫው ተቃውሞ ያሰከትላል በሚል የመርሀ ግብር ለውጥ ተደረገበት
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ እሁድ ለአባይ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ታስቦ በተዘጋጀው የሩጫ ፕሮግራም ላይ ገዥው ፓርቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊገጥመው ይችላል የሚል ሥጋት መፈጠሩን የኢሳት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሩጫ ፕሮግራሙ ቀደም ሲል ከመስቀል አደባባይ፣ በታላቁ ቤተመንግስት በኩል በፍልውሃ አድርጎ ወደ መስቀል አደባባይ ለመመለስ መርሃግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም ከጸጥታ ሥጋት ጋር በተያያዘ መነሻው መስቀል አደባባይ ...
Read More »በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ በሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲናዶስ፤ በአርሲ-አሰሳ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሙስሊሞች ላይ የኢህአዴግ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት የፈፀሙትን ግድያ አጥብቆ አወግዟል። ሲኖዶሱ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ግድያ እና አሁንም እየተፈፀመ ያለውን በደል ያወገዘው ሰሞኑን ያካሄደውን 33 ኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው። ሲኖዶሱ በዚሁ የአቋም መግለጫው በአሰሳ-መስጊድ የተፈፀመውን ግድያ ከማውገዝ በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »ካናዳ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ልትቀንስ ነው
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወግ አጥባቂው የካናዳ መንግስት ለውጪ እርዳታ ከሚሰጠው ገንዘብ ውስጥ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት 377 ሚሊዮን ዶላር ለመቀነስ መወሰኑን “ኦታዋ ሲቲዝን”ዘገበ። የካናዳ ዓለማቀፍ የልማት ፕሮግራም -ሲ.አይ.ዲ.ኤ፤ የሁለትዮሽ ፕሮግራሙን ከሚቀንስባቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ሆና መለየቷን የካናዳ ዓለማቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቤቭ ኦዳ ገልጸዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ ከምታገኘው እርዳታ ምን ያህል መጠን እንደሚቀነስባት የትብብር ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቱ አልገለጸም። እንደ ...
Read More »ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ ትሆናለች ተባለ
ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር አይኤም ኤፍን ጠቅሶ እንደዘገበው ኤርትራ በማእድን፣ በመሰረተ ልማት እና በእርሻው መስክ ባስመዘገበችው ውጤት ከምስራቅ አፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ አገር ትሆናለች። ኤርትራ በ7.5 በመቶ እንደምታድግ የተነበው አይ ኤም ኤፍ፣ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 5 በመቶ ብቻ ያድጋል ብሎአል። የመለስ መንግስት 11 በመቶ የኢኮኖሚ እደገት ማግኘቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ፣ የኤርትራ መንግስት በአንጻሩ ስለ አገሪቱ ...
Read More »አቶ ክፍሌ ስንሻው በማረሚያ ቤት አረፉ
ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በሀገር ክህደትና ህገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ አሲረዋል ተብለው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው በቃልቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክፍሌ ስንሻው በትላንትናው እለት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡ በዛሬው እለት አስከሬናቸው ከፖሊስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ ሚንሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ሄዷል ያሉን ምንጮቻችን፣ በማረሚያ ቤት በቂ ህክምና እና መድሃኒት እንዳያገኙ ሳንካ ...
Read More »በእነ አቶ አንዷለም አራጌ ላይ ሊሰጥ የነበረው ውሳኔ ተላለፈ
ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ዐቃቤ-ሕግ በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ከከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላትና ጋዜጠኞች ውስጥ በሀገር ውስጥ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን የሚከላከሉት ስምንት ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ለውሳኔ ዛሬ ጠዋት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቢቀርቡም ፍርድ ቤቱ በተለዋጭ ቀጠሮ ለሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ሰጥቶ አሰናብቷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ...
Read More »የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተቃውሞ ለአደረጉ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ
ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትናንት ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን ፆማቸውን በመዋል ተቃውሞ በማሰማት ላይ ላሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ። ተማሪዎቹ፤ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሙስሊም ሀይማኖታዊ መብቶቹን ለማስከበር እያደረገ ያለው ትግል የነሱም ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ፤ መብታቸው እስኪከበር ድረስ ከሙስሊም ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን እንደሚሰለፉ ገልጠዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ከዚህም ባሻገር መንግስት ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአርሲ-አሰሳ መስጅድ ሀይማኖታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ...
Read More »ኢህአዴግ መጅሊስ እንዲፈርስ ቢወሰንም ሙስሊሞቹ ግን ትግሉ ይቀጥላል ይላሉ
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተፈጠረበት ጫና ሃይማኖቱን በበላይነት ሲመራ የነበረውንና በመንግሥት የሚደገፈውን መጅሊስ እንዲፈርስ ባለፈው ሃሙስ ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በመጅሊስ የተጠሩ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች ከፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን ከሰኔ መጀመሪያ እስከ ሐምሌ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ መጅሊስ በምርጫ ይቋቋማል ...
Read More »