አቶ ክፍሌ ስንሻው በማረሚያ ቤት አረፉ

ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በሀገር ክህደትና ህገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ አሲረዋል ተብለው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው በቃልቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክፍሌ ስንሻው በትላንትናው እለት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

በዛሬው እለት አስከሬናቸው ከፖሊስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ ሚንሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ሄዷል ያሉን ምንጮቻችን፣  በማረሚያ ቤት በቂ ህክምና እና መድሃኒት እንዳያገኙ ሳንካ ሲደረግባቸው ህመማቸው በመባባሱ በመጨረሻው ፖሊስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው አልፏል ብለዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸው አቶ ክፍሌ እንደሻውን ወደ ጎጃም ሞጣ ወስደው ለመቅበር ቢፈልጉም ማረሚያ ቤቱ ቤተሰቦች ስለመሆናችሁ ከቀበሌ የድጋፍ ደብዳቢ እንዲያመጡ በማዘዙ ዘመዶቻቸውን  በመጉላላት ላይ መሆኑ ታውቋል።

አቶ ክፍሌ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሙከራ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ ከፍተና የሆነ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል።

በሌላ በኩል ደግሞ የመለስ መንግስት እነ ጄኔራል ተፈራ ይቀርታ እንዲጠይቁ የተለመዱ ሽማግሌዎችን ወደ ቃሊቲ መላኩ ታውቋል። የሽማግሌዎቹ ጥረት በምን ደረጃ ላይ መሆኑን ለማወቅ ባይችልም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የአማራ ተወላጅ  የጦር መኮንኖችን በመፍታት መንግስት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብአዴንን ጨምሮ ከአማራው ህዝብ እየተነሳበት ያለውን ተቃውሞ ለማብረድ ሊሞክር ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide