ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የደህንነት ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች አስወጋጅ ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላት የሆኑትን አህመዲን ጀበል እና ዑስታዝ አቡበከር አህመድን ለግማሽ ቀናት አስሮ ለቀቀ፡፡ የእሥሩ ምክንያት በመጪው እሁድ በአወሊያ መስኪድ ያዘጋጁትን የአንድነትና የመጅሊስ ይፍረስ ተቃውሞ ስብሰባን እንዲያቋርጡ ለማድረግ ነው ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡ ሁለቱ የኮሚቴ አባላት ለእሁድ ሕዝባዊ የጸሎትና የመጅሊስ ይፍረስ የተቃውሞ ዝግጅት የኮሚቴ ስብሰባ ...
Read More »የምርጫ ቦርዱ አቶ ተስፋዬ መንገሻ ከሃላፊነት ተነሱ
ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የምርጫ ቦርድ ዋና ጸሐፊ በመሆን ለገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ ውለታ የዋሉት አቶ ተስፋዬ መንገሻ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ በተለይ ኢህአዴግ በ1997ቱ ምርጫ ከፍተኛ ሸንፈት ባጋጠመው የጭንቀቱ ወቅት በምርጫ ቦርዱ የተቀነባበረ ማጭበርበር በማድረግ፣በድጋሚ ምርጫዎች በቶ በመቶ የተሸነፉ ባለሥልጣናትን በአስደናቂ ሁኔታ መቶ በመቶ እንዲያሸንፉ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ ከምርጫ 97 በኃላ ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ ሕመም ...
Read More »አቶ ሽመልስ ከማል ዳግም ተጋለጡ
ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ቃል አቀባይ ነኝ የሚሉት አቶ ሽመልስ ከማል ስካይፒንና ሌሎችን የኢንተርኔት የመገናኛ ዘዴዎችን የሚከለክል ህግ አላወጣንም በማለት አለም የሚያውቀውን ሀቅ ሲክዱ ቢቆዩም፣ ትናንት ቃል በሚያቀብሉለት መንግስት ተጋልጠዋል። የሕወሃት/ኢሕአዴግ ፓርላማ በትናንት ሃምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ውሎው ያፀደቀው ይህ አዲስ አዋጅ፣ ቀደም ሲል የወጣውን አፋኝ ሕግ ሙሉ ለሙሉ የሚሰርዝና፣ የድምጽና የፋክስ መልዕክትን ጨምሮ ስካይፒና ...
Read More »ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ዙሪያ ለዓለም ባንክ ደብዳቤ ጻፈ
ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዓለም ባንክ፤ ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የኤሌክትሪክ መስመር ለመዘርጋት በሚል እየሰራች ላለው የአሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ገንዘብ ከመለገሱ በፊት፤ የፕሮጀክቱ አካባቢው እንዳማይጎዳና የነዋሪዎች ህይወት እንደማይናጋ ሊያረጋግጥ ይገባል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች አሣሰበ። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች ይህን ያለው፤ ጎዳዩን አስመልክቶ ትናንት ለዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ለጂም ዮንግ ኪም በፃፈው ደብዳቤ ላይ ነው። ...
Read More »ለአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ የተጠራው ፓርላማ የቴሌን ህግ አጸደቀ
ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-99 ነጥብ ስድስት በመቶ በአንድ ድርጅት አባላት የተሞላው ፓርላማ ለአስቸኳይ ልዩ ጉባኤ የተጠራው አዲሱንና አወዛጋቢውን የቴሌ ህግ ለማጽደቅ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ዘጋቢያችን እንዳለው በጥሪው ላይ አስቸኳይና ልዩ የተባለው ፓርላማው ካለፈው ሰኔ ሰላሳ ቀን ጀምሮ እንደተዘጋ በመቆጠሩ ነው። የፓርላማ አባላቱ ፓርላማው እንደተዘጋ የማያውቁ ሲሆን፣ የዛሬው ልዩ ስብሰባ የተጠራው የፓርላማ አባላቱ እረፍት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ...
Read More »አፈናው ቢጨምርም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ግን ተቃውሞአቸውን አጠናክረዋል
ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ረመዷን ፆም ከመግባቱ በፊት በአዲስ አበባ ትልቅ የ“ድምፃችን ይሰማ” የአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግና በፆም ወቅትም ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ በመጪው እሁድ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ተኩል በአወሊያ መስኪድ ቅጥር ጊቢ በሚካሄደው ህዝባዊ አንድነትና የተቃውሞ ስብሰባ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦችና ...
Read More »የፍትህ ዋና አዘጋጅ ደኅንነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል
ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳምንታዊው ፍትህ የአማርኛ ጋዜጣና በዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የግል እንቅስቃሴ ላይ የደህንነት ኃይሎች የሁለት ቀናት የሃያ አራት ሰዓታት ግልጽ ክትትል ማድረጋቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡ በጋዜጣው የኢሜል አድራሻም ከአልሸባብ ለዋና አዘጋጁ የተላከ የሚያስመስል ቁጥር 2 የፈጠራ ደብዳቤ ከሰሞኑ ተልኳል፡፡ ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን እና እሁድ ሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጋዜጠኛ ...
Read More »ግራ የተጋባው ፓርላማ ነገ ለልዩ ስብሰባ ተጠራ
ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመዝጊያው ጊዜ እስከዛሬ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የተራዘመው ፓርላማ ፣ ነገ ረቡእ ለልዩ ስብሰባ ተጠርቷል። በነገው ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይገኙ እንደሆን ለምንጫችን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ፣ “እስካሁን ድረስ ይገኛሉ የሚል ፍንጭ አለመሰማቱን፣ ይሁን እንጅ ይገኛሉ ብለው እንደማያስቡ” ተናግረዋል። በፓርላማው አሰራር መሰረት አቶ መለስ በተገኙበት የሚቀጥለው አመት በጀት ለፓርላማው ተልኮ ...
Read More »የቴልኮም አዋጅ ነገ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል
ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነገው ልዩ የፓርላማ ስብሰባ ላይ አወዛጋቢው የቴልኮም አዋጅ እንደሚጸድቅ ለማወቅ ተችሎአል። በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር ከፍተኛ ውግዘት የደረሰበት አዲሱ የቴልኮም አዋጅ እንዲጸድቅ የሚደረገው ምንም አይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት ነው። ስካይፕ እና ሌሎች በኢንተርኔት የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ማስተናገድ በወንጀል የሚአስከስሰውና እስከ አስር አመትና እስከ 100 ሺ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ከጸደቀ፣ የመለስ መንግስት ማንኛውንም ዘመናዊ ...
Read More »የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ
ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኮምቦልቻ ከተማ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ደማቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍለዉ የነበሩት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሼህ መከተ ሞሄ በፖሊስ ታፍነዉ መታሰራቸዉን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘግቧል። ሼህ መኸተ ሞሄ የታሰሩት ፕሮግራሙን ጨርሰዉ ወደ ማረፊያ ሆቴላቸዉ ከገቡ ቡሁዋላ በበርካታ ፖሊሶች ታፍነው ነው። ከሸህ መከተ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ፕሮግራም ላይ ከተካፈሉት መካከል፤ ...
Read More »