የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኮምቦልቻ ከተማ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ደማቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍለዉ የነበሩት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሼህ መከተ ሞሄ በፖሊስ ታፍነዉ መታሰራቸዉን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘግቧል።

ሼህ መኸተ ሞሄ የታሰሩት ፕሮግራሙን ጨርሰዉ ወደ ማረፊያ ሆቴላቸዉ ከገቡ ቡሁዋላ በበርካታ ፖሊሶች ታፍነው ነው።

ከሸህ መከተ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ፕሮግራም ላይ ከተካፈሉት መካከል፤  ታዎቂዉ “ዳኢ” እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነዉ ኡስታዝ ያሲን ኑሩም በፖሊሶች እየተፈለገ መሆኑን ወኪላችን ያጠናቀረው ዘገባ ያመለክታል።

በአሁኑ ጊዜ  የአካባቢው ፖሊስ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን ለማሰር ከተማዋን እያሰሰ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል!!

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide