የኦሮሞ ነጸናት ግንባር በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አደረገ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብርጋዲየር ጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የአሮሞ ነጸናት ግንባር ባለፈው ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 6 ቀን 2012 በቶሮንቶ ካናዳ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አድረገ። በዚህ በቶሮንቶ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት የግማሽ ቀን ስብሰባ ላይ፤ የድርጅቱ የበላይ አመራር አካላት፡ ማለትም ብርጋዲየር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ ከአስመራ በስልክ፡ ዶ/ር ኑሮ ደደፎና የድርጅቱ ቃል አቀባይ ...

Read More »

እስራኤል የመጨረሻዎቹን ቤተ-እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ልታጓጉዝ ነው

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል መንግስት 2 ሺህ 200 ቤተ እስራኤላውያንን እ.ኤ.አ እስከ ማርች 2014 ድረስ ከኢትዮጵያ  ለማንሳት እንዳቀደ አስታወቀ። እነኚሁ ከኢትዮጵያ የሚጓጓዙት ቤተ እስራኤላውያን  የመጨረሻዎቹ እንደሆኑ የገለፀው የእስራኤል ካቢኔ፣ የሚያስፈልጋቸውን መጠለያና ሌላም ነገር ለማሟላት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመደበ ሲሆን፣ በየወሩ 250 ቤተ እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ለማምጣት እንዳቀደ ገልጿል ። በተለምዶ “ፈላሻ-ሙራ” በመባል የሚታወቁት እነኚሁ ኢትዮጵያዊያን ይሁዲዎች፣ ...

Read More »

አዲስ አበባ በነዳጅ እጥረት ተጨናነቀች

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ስራቸውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አቁመዋል። በዚህም የተነሳ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ የከተማዋ ትራፊክ ከወትሮው በባሰ ተጨናንቋል። አብዛኞቹ ታክሲዎች በነዳጅ እጥረት ስራቸውን አቋርጠዋል። የችግሩ መንስኤ የአቅርቦት ይሁን የስርጭት አልታወቀም፣ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ነዳጅ ከሱዳን ማስገባት ካቆመችበት ጊዜ ጀምሮ የነዳጅ አቅርቦቱ ችግር እየገጠመው ...

Read More »

ሚኒስትሩ ፤ በቴሌ ሠራተኞች ጠንካራ ተቃውሞ ገጠማቸው

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በአቶ  ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሰብሳቢነት የቴሌ ሠራተኞች በወቅቱ አገራዊ ጉዳይ ትናንት የጀመሩት ውይይት፤ በከፍተኛ ተቃውሞ እየቀጠለ እንደሚገኝ በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ዘጋቢ አመለከተ። እጅግ በርካታ የቴሌ ሠራተኞች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎቹ  ከሰነዘሯቸው ተቃውሞዎች አንዱ፤ “የኮንዶሚኒየም ቤት ለደሀው ህዝብ እንደሚሠራ ስትናገሩ ከቆያችሁ በሁዋላ አሁን ሲጠናቀቅ ለሀብታሞችና ለተወሰኑ ብሔር አባሎች እየመረጣችሁ መስጠታችሁን ደርሰንበታል” ...

Read More »

የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም ሚስጢር እንደሆነ ነው

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርላማ አባላት ግራ ተጋብተዋል፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል ፣ አንዳንድ መረጃዎች አቶ መለስ የወራት እድሜ እንዳላቸው ይጠቁማሉ ዝርዝሩ ኢሳት የፓርላማው መዝጊያ በአንድ ሳምንት እንደሚራዘም፣ ምክንያቱ ደግሞ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ችግር እንደሆነ ከዘገበ በሁዋላ ፣ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ የመላው ኢትዮጵያውያን የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። በኢህአዴግ ዙሪያ የተሰባሰቡ አባላት ሳይቀሩ ግራ ተጋብተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ ...

Read More »

በደርግ ዘመነ መንግስት የነበረውን ጥበባዊ አሻራ ለማስቃኘት ታሰቦ የተከፈተው የሥዕል ኤግዚቢሸን በኢቲቪ እንዳይተላለፍ ታገደ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኤግዚቢሸኑ ዜና በኢቲቪ ከተዘገበ በኃላ እንዳይተላለፍ የታገደው ያለፈውን ሥርዓት የሚያንቆለጻጽስ ነው በሚል ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስክንድር በጎሲያን ሥነ ጥበባት ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ትምህርት ቤት ከ1967 እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ተማሪዎቹ ከሠሯቸው ልዩ ልዩ ሥዕሎች መካከል የተመረጣቸውን ሥዕሎች በሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለእይታ አብቅቷል፡፡ ዝግጅቱን አስመልክቶ የተዘጋጀው ካታሎግ በደርግ ዘመን የመጀመርያዎቹ ዓመታት የሥዕል ...

Read More »

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሰኔ 24 እስከ 26; 2004  በሰሜን አሜሪካ፥ ዳላስ ከተማ ከአርባ ከተሞችና ከተለያዩ አህጉራት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ጉባኤ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና የቀረቡ ሰነዶች ላይ ሶስት ቀናት የፈጀ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት ማቋቋሙን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ጉባኤው  “የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት፥ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር ሁሉን አቀፍ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት መውረዱን ብሉም በርግ ዘገበ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ ብሄራዊ ስታትስቲክስን ጠቅሶ እንደዘገበው በሰኔ ወር ውስጥ የዋጋ ንረቱ ከ25 በመቶ ወደ 21 በመቶ ዝቅ ብሎአል። የምግብ ዋጋዎች በአንጻሩ ከአምናው ጋር ሲተያይ 21 በመቶ ከፍ ብሎአል። የአቶ መለስ መንግስት በሰኔ ወር የዋጋ ንረቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርደው ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጅ አቶ መለስ ይህን ማድረግ እንደማይቻል አምነው በመስከረም ወር ግሽበቱን ወደ አንድ ...

Read More »

ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ የመንግስትን አካሄድ እየተቃወመ ነው

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመብት ጥያቄያቸውን እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ያለፉትን ስድስት ወራት ያሳለፉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፣ መንግስት ጥያቄያቸውን ወደ ጎን በማለት አጠቃላይ ሂደቱን እሱ በሚፈልገው መንገድ ለማስተናገድ መሞከሩ ሙስሊሙን እያስቆጣ ነው። በትናንት የአርብ ጁምዓ ጸሎት በአንዋር መስኪድ እና ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጊድ የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መንግስት ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ ለማስተናገድ እየተጓዘበት ያለው መንገድ ችግሩን ከማወሳሰብ ...

Read More »