አቶ መለስ ቶሎ ስራ አይጀምሩም ተባለ

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮምኒኬሸን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን አቶ መለስ ሕክምናቸውን አጠናቀው በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ፣ከሳቸው ጋር በተያያዘ በኢህአዴግ ውስት ሸኩቻ ተፈጥሯል የሚባለው ውሸት መሆኑን ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች የቀረቡላቸውን ጥያቁዎች ማለትም አቶ መለስ በምን ሕመም እንደተያዙ፣የት ሆስፒታል እየታከሙ እንደሆነ፣በአሁኑ ሰዓት የት እንዳሉ “የቤተሰባቸውና የግላቸው ጉዳይ ነው” በሚል ምላሸ ከመስጠት ...

Read More »

በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጠው በሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ 3 የልማት ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፤ ከትናንት በስቲያ ከታሰሩት መካከል ደግሞ፣ የግብርና ሰራተኞች የሆኑት አቶ ዳዊት ኡጋሞና አቶ በለጠ በልጉዳ፣ የመዘጋጃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዘሪሁን፣ መምህር ተስፋየ ተሻለ፣ መምህር አብዮት ዘሪሁን፣ መምህር በፍቃዱ ዱሞ፣ መምህር ለገሰ ገሰሰ፣ መምህር ዶልቃ ዱጉና እና ...

Read More »

በቦረና ዞን በገብራና በቦረና መካከል በተነሳ ግጭት የሟቾች ቁጥር 45 መድረሱ ታወቀ

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ የኦሮሞ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ከግጦሽ መሬት ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ ባለፈው ሳምንት በኢሳት የቀረበው ዘገባ ፣ የችግሩን ትክክለኛ መንስኤ አላሳየም በሚል የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኣካባቢው ችግር የዘር ፖለቲካው የፈጠረው ነው ይላሉ ነዋሪዎች ( ) ገብራዎች በ1997 ምርጫ ወቅት ቅንጅትን መምረጣቸውም ለቅጣት እንደዳረጋቸው ተወላጆች ይገልጣሉ። ኢሳት ባለፈው ሳምንት በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ...

Read More »

በግብጽና በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ዛሬ በካይሮ ከተማ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የመለስ መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን አውግዘዋል። ኢትዮጵያውያን ” የሙስሊሙና የክርስቲያኑ አገር ናት፣ ሁላችንም አንድ ሆነን መንግስት መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን፣ ለመብት መታገል አክራሪነት አይደለም” የሚሉ መፈክሮችን አስምተዋል። በጀርመን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በፍራንክፈርት ከተማ ባካሄዱት የተቃውሞ ...

Read More »

የአቶ መለስ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 2 ሳምንታት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቦ የቆየው የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተሉ ታዘዙ የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ የአመራር አባልን በመጥቀስ እንደዘገበው  የፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት አባላት የአቶ መለስን የጤና ሁኔታ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ወይም በዋና ...

Read More »

መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈል ከፍተኛ ሩጫ ላይ ነው

ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ የተጀመረው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ መንግስት አንዳንዱን በግድ ሌላውን በመደለል በእየ ክፍለሀገሩ የሚገኙ ሙስሊሞችን ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን እንዲያወግዙ እያደረገ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የሙስሊም መሪ ለአዲስ አበባው ወኪላችን እንደገለጡት፣ መንግስት በ1997 ዓም ቅንጅትን ከፋፍሎ  ለመምታት የተጠቀመብትን ዘዴ በሙስሊሙ ላይ ተግባራዊ እያደረገ ነው። በየክፍለሀገሩ የሚገኙ ሙስሊሞች የአወልያውን ...

Read More »

የሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ታሰሩ

ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የ አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ገንዘብ ይዘው ሲወጡ ተይዘው መታሰራቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ መሐሙድ ፤በወረዳ 17 ወርቁ ሕንፃ አጠገብ ከሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ግምቱ ከሃምሳ እስከ መቶ ሺ ብር የሚገመት የታሰረ ገንዘብ እና ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2005 በጀት እያነጋገረ ነው

ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2005 በጀት ዓመት ለአስሩ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በዓላማ ላልተገደበ ተግባር ማወሉ እያነጋገረ ነው፡፡ የአቶ ኩማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ለ2005 በጀት ያጸደቀው 16 ቢሊየን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ክፍለከተሞች እንደፈለጉት ሊመነዝሩት የሚችሉት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ባልተለመደና ከበጀት አያያዝና አጸዳደቅ ፍጹም በተለየ መልኩ ...

Read More »

በትግራይ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ ከመቀሌ በላከው ዘገባ እንዳመለከተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የክልሉ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ የአቶ መለስ ዜናዊ ህመም ነው። ሁለት አይነት አስተያየቶች ይቀርባሉ የሚለው ዘጋቢያችን፣ አንደኛው ወገን አቶ መለስ አርፈዋል ብሎ የሚያምን ሲሆን ሌላኛው ወገን ግን ህመማቸው ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ብሎ ያምናል። የአቶ መለስን ህመም ተከትሎ በክልሉ ይህ ነው የሚባል የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የጠቀሰው ...

Read More »

በመንግስት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል ያለው ፍጥጫ እየጨመረ ነው

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ ድምጻችን ይሰማ በማለት ላለፉት ተከታታይ ወራት ተቃውሞ ሲያሰሙ የቆዩ ሙስሊሞች፣ አርብ እለት የመንግስት ታጣቂዎች በአወልያ የፈጸሙትን ግድያ እና ድብደባ በመቃወም፣ እሁድ እለት ከመንግስት ፈቃድ ወጭ የሰደቃና የአንድነት ዝግጅት ማድረጋቸው መንግስትን በእጀጉ ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል። ባለፈው አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ፣ በጎጃም እና በጅማ መስመሮች ወደ አዲስ አበባ ይጓዙ የነበሩ ...

Read More »