የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ከበር መመለሳቸው ተሰማ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው አርብ 70 የሚሆኑ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። በዛሬው እለት ደግሞ 8 የአመራር አባላት አራዳ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ወዲያውኑ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል። የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ድምጻችን ይሰማ በማለት ጥያቄ ባቀረቡ ሙስሊሞች ላይ የጅምላ እስር እና ድብደባዎችን ፈጽመዋል።  ትናንት እሁድና ዛሬ ሰኞ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ...

Read More »

መድረክ ወደ ግንባር የተሸጋገረው ከአቶ መለስ ህመም ጋር ተያይዞ አለመሆኑን ዋና ጸሀፊው ገለጡ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ /ኦህኮ / ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን / ፣ አረና ትግራይ ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ናቸው ባለፈው ቅዳሜ በጋራ ግንባር የመሰረቱት። አቶ ጥላሁን እንዳሻው ሊቀመንበርነት ፥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዶክተር ...

Read More »

አቶ አባዱላ ገመዳ የዘንድሮ ፓርላማ መራዘም ከጠ/ሚኒስትሩ ሕመም ጋር አይያያዝም አሉ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰኔ 30 መዘጋት የነበረበት የዘንድሮ ፓርላማ የሥራ ፕሮግራም መራዘም እንዲያው ልማድ ሆኖ እንጂ ከጠ/ሚኒስትር መለስ ሕመም ጋር የሚያያይዘው አንዳችም ነገር የለም ሲሉ አቶ አባዱላ ገመዳ ገለጹ፡፡ የፓርላማው አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ዛሬ በጽ/ቤታቸው የፓርላማውን ዓመታዊ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ የፓርላማው የስራ ጊዜ መራዘም ከጠ/ሚኒስትሩ ጤንነት ጋር ይያያዝ እንደሆን ከጋዜጠኞች ተጠይቀዋል፡፡ እሳቸውም ...

Read More »

በመርካቶና አካባቢዋ ግጭት ተነሳ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብና በኢህአዴግ መካከል የተፈጠረው የመብት ጥያቄ ውዝግብ ተካሮ  በፖሊሶች ላይ ድንጋይ የወረወሩ ሲሆን የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶ የጥይትና አስለቃሽ ጭስ ምላሸ የሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በርካታ ሰዎች የመፈንከት፣ የመደብደብ እና በትልልቅ ኦራል ካሚዮን እየተጫኑ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል፡፡ በግጭቱ ላይ በመርካቶ አንዋር መስኪድ ዙሪያ፣ ...

Read More »

ፍትህ ጋዜጣን ማገድ የአገሪቱ ሁኔታ ወደ አደገኛ ሁኔታ መሄዱን የሚያመላክት ነው ሲል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተናገረ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ነው። መንግሥታዊው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ሃሙስ ምሽት ሳንሱር አድርጎ አላትምም ብሎ ያቋረጠውን የፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 5 ቁጥር 197 ፣ ከፌዴራል ጸረ ሽብር ግብረይል፣ ዐቃቤ- ሕግ፣ የደህንነት ኃይሎች እና ከፍትህ ሚንስትር ተወካዮች ጋር ከተነጋገረና ይዘቱን ካስገመገመ በኋላ ትላንት ከቀኑ ...

Read More »

መድረክ ወደ ግንባር ተሸጋገረ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ /ኦህኮ / ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን / ፣ አረና ትግራይ ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ናቸው ዛሬ በጋራ ግንባር የመሰረቱት። አቶ ጥላሁን እንዳሻው ሊቀመንበርነት ፥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዶክተር መረራ ...

Read More »

ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን አስወግደው ወደ ውይይት እንዲመጡ ኢትዮጵያውያን ጠየቁ

ሐምሌ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ዜጎች የአቶ መለስ ዜናውን ህመም ተከትሎ ለኢሳት በሰጡት አስተያየት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነታቸውን አስወግደው ወደ ውይይት መምጣት ግድ ይላቸዋል ብለዋል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ የሆነው ወጣቱ ጸሀፊ ዳንኤል ተፈራ እንደገለጠው ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ያለው ጉጉት ሊረካ የሚችለው መነጋገር ሲቻል ብቻ ነው ብሎአል። በዶ/ር ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መካከል የተወሰኑት ታስረዋል

ሐምሌ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢያችን በላከው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሙስሊም መሪዎችን መታሰር በይፋ ከዘገበ በሁዋላ በርካታ መሪዎች ቤቶች ሲፈተሹ አድረዋል። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ መሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ቢሆንም፣ ከጀሚል ያሲን፣ ሼህ ሱልጣን አማን እና የቄራ መስጊድ ምክትል ኡዝታዝ ከሆኑት ሰኢድ አሊ በስተቀር ሌሎችን ፈተዋቸዋል። በዛሬው እለት ለንባብ የሚበቁት ሰለፍያ እና ሰውቱል እስላሚያ የተባሉት የሙስሊም ጋዜጦች ...

Read More »

ሰመጉ የእስረኞቹ ጉዳይ ያሳስበኛል አለ

ሐምሌ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ ኢሰመጉ የአሁኑ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) በፖለቲካ መሪዎችና በጋዜጠኞች ላይ በቅርቡ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ያሳስበኛል አለ፡፡ ሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው የጸረ ሸብር ሕጉን በመተላለፍ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኃላ ጉዳያቸው በፍ/ቤት ሲታይ የቆየው በእነአንዱዓለም አራጌ ስም የተከፈተውም ሆነ ቀደም ሲል በተለያዩ ፋይሎች የተፈረደባቸው ኢትዮጽያዊያን ጉዳይ ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር እጅግ አድርጎ ...

Read More »

ታለቁ የፖታሽ ኩባንያ ኢትዮጵያን ለቆ ወጣ

ሐምሌ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ የዜና ሽፋን አግኝቶ የነበረውና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የፖታሽ ላኪ አገር ያደርጋታል ተብሎ የተነገረለት የአውስትራሊያው  ቢኤች ቢልተን ኩባንያ የአፋርን ክልል ለቆ ወጥቷል። ኩባንያው አካባቢውን ለቆ እንደሚወጣ ለመንግስት ባለስልጣናት መናገሩን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኩባንያው ከኢትዮጵያ የወጣበትን ምክንያት አላስታወቀም። በቅርቡ የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት በአፋር አካባቢ ላሉ አለማቀፍ ኩባንአዎች የተቃውሞ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT ...

Read More »