መድረክ ወደ ግንባር ተሸጋገረ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ /ኦህኮ / ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን / ፣ አረና ትግራይ ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ናቸው ዛሬ በጋራ ግንባር የመሰረቱት።

አቶ ጥላሁን እንዳሻው ሊቀመንበርነት ፥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዶክተር መረራ ጉዲናን ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፣ አቶ ገብሩ አስራትን ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ሞጋ ፍሪሳን ዋና ፀኃፊ አድርጎ ግንባሩ መርጧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide