በግብጽና በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ዛሬ በካይሮ ከተማ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የመለስ መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን አውግዘዋል። ኢትዮጵያውያን ” የሙስሊሙና የክርስቲያኑ አገር ናት፣ ሁላችንም አንድ ሆነን መንግስት መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን፣ ለመብት መታገል አክራሪነት አይደለም” የሚሉ መፈክሮችን አስምተዋል።

በጀርመን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በፍራንክፈርት ከተማ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ደግሞ በዋልድባ አካባቢ የሚሰራው ስራ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ሰሞኑን አቡነ ጳውሎስ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ትእዛዝ ቢያስተላለፉም፣ በጀርምን የሚኖሩ ቀሳውስት ሳይቀር፣ የአቡነ ጳውሎስን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በማለት በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide