በቦረና ዞን በገብራና በቦረና መካከል በተነሳ ግጭት የሟቾች ቁጥር 45 መድረሱ ታወቀ

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሁለቱ የኦሮሞ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ከግጦሽ መሬት ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ ባለፈው ሳምንት በኢሳት የቀረበው ዘገባ ፣ የችግሩን ትክክለኛ መንስኤ አላሳየም በሚል የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የኣካባቢው ችግር የዘር ፖለቲካው የፈጠረው ነው ይላሉ ነዋሪዎች ( )

ገብራዎች በ1997 ምርጫ ወቅት ቅንጅትን መምረጣቸውም ለቅጣት እንደዳረጋቸው ተወላጆች ይገልጣሉ።

ኢሳት ባለፈው ሳምንት በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ችግር 20 ሰዎች መገደላቸውን የገለጠ ቢሆንም፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የማቾች ቁጥር 45 ነው ይላሉ።

ግጭቱን ተከትሎ የዞኑ ካቢኔ አባላትና  የወረዳው አስተዳዳሪ ታስረዋል። መንግስት ግጭቱን ያስነሳችሁት እንናተ ናችሁ በሚል ባለስልጣናቱን ማሰሩን ምንጮች ተናግረዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide