ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለቤታቸው የታሰሩባቸው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፦”ይቅርታ ጠይቁ” በመባላቸውን በመጥቀስ፦” የሠራሁት ስህተት ስለሌለ የምጠይቀው ይቅርታ የለም” አሉ። ባለቤቴ ከህፃናት ልጆች ተነጥላ ትክክለኛ ባልሆነ ማስረጃ ታስራብኛለች ሲሉም አቤት አሉ። ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ የባለቤታቸውን መታሰር አስመልክቶ በኢትዮ ቻነል እና በሰንደቅ ጋዜጦች ለወጡት ዜናዎች መልስ በሰጡበትና በዛሬው የ ኢትዮ ቻነል ጋዜጣ ላይ በታተመው ጽሁፋቸው ...
Read More »ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በኩዌት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እራሷን አጠፋች
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አረብ ታይምስ ትናንት ባወጣው ዘገባ እንደገለፀው ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊቷ ትሰራበት የነበረው ቤት ውስጥ ራሷን የመግደል ሙከራ ስታደርግ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ስነልቦና ሕክምና እንድትወስድ ተደርጋ ነበር። ሆኖም ከሆስፒታሉ ስትወጣ “ጃሃራ” በሚባል ስፍራ ወደሚገኘው “አል-ነኢም” ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ በመታሰር በምርመራ ላይ ሳለች፤ የእስር ቤቱ መታጠቢያ ቤት ውስጥ አድርጋው በነበረው ሂጃብ የራሷን ሕይወት አጥፍታ ተረኛው ...
Read More »በለንደን እየተካሄ ባለው 17ኛው ኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ 10፣000 ሜትር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አጠለቀች
ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ውድድሩ ከመካሄዱ በፊት ኬንያውያን ወርቁ የእነሱ እንደሆነ ደምድመው ለተለያዩ ሚዲያዎች ብዙ ብለዋል። በተለይ በዳጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 5 000 እና በ 10 000 የድርብ ወርቅ ሜዳል ባለቤት የሆነችውና በትናንት ምሽቱ የ 10000 ሜትር ውድድር ሦስተኛ የወጣችው ቪቪያን ቸሩዮት ወድድሩ ከመካሄዱ በፊት፤ ወርቁ የእሷ እንደሆነ በእርግጠኝነት በማወጅ፦”ኬንያውያን ከአሁን ጀምረው መጨፈር ይችላሉ” ነበር ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ቀጥለው ዋሉ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊም ማህበረሰብ ዛሬ ከቀኑ 5 ሰአት ተኩል ጀምሮ በአንዋር መስጊድ በመሰባሰብ የአርብ ስገደት ካደረጉ በሁዋላ ፣ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ቀጥለው ውለዋል። ቁጥራቸው ከ5 መቶ ሺ በላይ ሙስሊሞች ፣ የሚወርደው ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው ፣ ከጸሎት በሁዋላ ለደቂቃዎች ነጭ ማህረብ ጨርቅ ፣ ነጭ ሶፍት ወረቀት በማውለብለብ፣ ...
Read More »የሱዳን የደህነት አባላት የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅትን መሪ ልጅ አሰሩ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰራዊት አባላት ጋር ድርድር በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። ሱዳን አገር የሚገኙ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት የድርጅቱ ሊቀመንበር ባልተገኙበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ከመንግስት ጋር ድርድር አድርገዋል። መንግስት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ዩሱፍ ሀሚድ ወደ አገር ከገቡ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል መግባቱን ፣ ይሁን እንጅ ...
Read More »የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እስር ወደ አምስት ዓመት ዝቅ አለ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የሰጠውን የ14 አመት ጽኑ እስራት እና የ33 ሺ ብር የቅጣት ውሳኔ፣ እስካሁን የታሰረችው አንድ አመት ከአንድ ወር ታሳቢ ተደርጎ ወደ 5 አመት ዝቅ እንዲል ወስኗል። የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ የኢህአዴግ ቀይ እስክርቢቶ የተሰኘ መጽሀፍ ነገ ሀምሌ 28 ...
Read More »የኢትዮ ቻነል እና የሳምሶን ማስታወቂያ ድርጅት ባለቤት የሆነው ሳምሶን ማሞ ከነ ባለቤቱ ታሰረ
ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሳምሶን አድቨርታይዚንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ እና የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ አሳታሚ የዜድ ፕሬስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘውድነሽ ታደሰ ባለፈው ሐሙስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ወደ 6 የሚሆኑ መለዮ የለበሱና ሲቪል የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞን አስገድደው የያዙት ሐሙስ ማለዳ ወደ ቢሮው በሚገባበት ወቅት ነበር፡፡ ...
Read More »የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ከአገር ተሰደደ
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል የወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለው፣ በክልሉ ውስጥ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ ያተረፈውና ወጣቱን ለለውጥ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ስራ መስራቱ የሚነገርለት ወጣት ዘመነ ካሴ እንዲሁም የህግ ምሩቃን የመሰረቱት የአባይ ፍሬዎች ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ከፍያለው ጌጡ ከገዢው ፓርቲ የደህንነት ሰዎች ክትትል አምልጠው ወደ ሶስተኛ አገር ተሰደዋል። ወጣት ዘመነና ወጣት ከፍያለው በስደት ካሉበት ...
Read More »በጋምቤላ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርና ሌሎች 4 ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት ሁለት ወራት በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች እንዲሁም የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን ኩባንያ ሰራተኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ፣ ከታጣቂዎች ጋር በመሆን ጥቃቱን አስፈጽመዋል የተባሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ያለመከሰስ መብታቸው በክልሉ ምክር ቤት እንዲነሳ ተደርጓል። ኮሚሽነሩ ያለመከሰስ መብታቸው ቢነሳም ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አለመታሰራቸው ታውቋል። የክልሉ የንግድ ቢሮ ሀላፊና ምክትላቸው ፣ የፋይናንስ ቢሮ ሀላፊዎች ...
Read More »“አገሪቷ በማን እየተመራች እንደሆነ አለመታወቁ አሣስቦኛል” ሲል መኢአድ ስጋቱን ገለጸ
ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ጊዜ አገሪቷን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ናቸው መባሉ እንዳልተዋጠለት እና በትክክል ይች አገር በማን እየተመራች እንደሆነ አለመታወቁ እንዳሣሰበው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ገለጸ። ይህ የመኢአድ ስጋት የተገለጸው፤ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት እንደሌሉ የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ ባሉበት ባሁኑ ጊዜ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ...
Read More »