በጋምቤላ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርና ሌሎች 4 ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፉት ሁለት ወራት በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች እንዲሁም የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን ኩባንያ ሰራተኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ፣ ከታጣቂዎች ጋር በመሆን ጥቃቱን አስፈጽመዋል የተባሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ያለመከሰስ መብታቸው በክልሉ ምክር ቤት እንዲነሳ ተደርጓል።

ኮሚሽነሩ ያለመከሰስ መብታቸው ቢነሳም ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አለመታሰራቸው ታውቋል።

የክልሉ የንግድ ቢሮ ሀላፊና ምክትላቸው ፣ የፋይናንስ  ቢሮ ሀላፊዎች  ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ሀላፊዎች ለእስር የተዳረጉት ከመምህራን ደሞዝ ጋር በተያያዘ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት በርካታ የክልሉ ባለስልጣናት እንደሚታሰሩ ታማኝ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘጋቢያችን ገልጧል።

እንዲሁም በትናንትናው እለት በእናሬ ወረዳ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ሰዎቹ የተገደሉት በወረዳው ነዋሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሎአል። ሁለቱ ሟቾች በጋምቤላ ከተማ በዛሬው እለት የቀብር ስነስርአታቸው ተፈጽሟል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide