የሱዳን የደህነት አባላት የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅትን መሪ ልጅ አሰሩ

ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መንግስት ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰራዊት አባላት ጋር ድርድር በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር።

ሱዳን አገር የሚገኙ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት የድርጅቱ ሊቀመንበር ባልተገኙበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ከመንግስት ጋር ድርድር አድርገዋል። መንግስት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ዩሱፍ ሀሚድ ወደ አገር ከገቡ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል መግባቱን ፣ ይሁን እንጅ አምባሳደሩ ማንኛውም ድርድር በሶስተኛ አገር መሆን አለበት በማለት ጠንካራ አቋም በመያዛቸው በድርድሩ አለመገኘታቸውን አምባሳደሩ ለኢሳት ገልጠዋል።

የትግል ጓዶቻቸው መሪው ባይሄዱም ልጃቸውን እንዲልኩላቸው ጠይቀዋቸው እንደነበር አምባሳደሩ ገልጠዋል። ልጃቸው ሀሊድ የሱፍ ሀሚድ ለእረፍት ወደ ሱዳን በተጓዘበት ወቅት የኢትዮጵያ የደህነት ሀይሎች በደማዚን ክፍለሀገር ወስደው እንዳሰሩት ተናግረዋል።

የደማዚን ክፍለሀገር አስተዳዳሪ የሆኑትን አሊህዲ ቡሽራን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ፣ አስተዳዳሪው ለማላውቀው ሚዲያ መረጃ መስጠት አልፈልግም በማለት መልሰዋል።

አምባሳደር ዩሱፍ ከወራት በፊት ሰፊ ቃለምልልስ ለኢሳት መስጠታቸው ይታወሳል።

_____________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide