በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ በእገታው ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ታሰሩ በአማራ ክልል የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪዎች፣ የሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ባለስልጣናትና ሌሎች የክብር እንግዶች ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ መንገድ ተረክበዋል በማለት በአካባቢው ነዋሪዎች መታገታቸውን ሰንደቅ ዘገበ። እገታውም በድርድርና ውይይት ከተፈታ በኋላ መንገድ ዘግተዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል። ...

Read More »

ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መፈረጅ ነው ተባለ

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደመፈረጅ ነው” ሲሉ የጅማ ሀገረ-ስብከት  ሊቀ-ጳጳስ ተናገሩ። ብጹዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ይህን ያሉት፤   የጅማ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ ጉባኤ ሰሞኑን  የ2004 ዓ.ም. ዕቅድና ክንውንን ለመገምገም እና የ2005 ዓ.ም. ዕቅድን ይፋ ለማድግ በጠራው ስብሰባ ላይ ነው። የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ማህበረ-ቅዱሳንን በተደጋጋሚ ፦” በአክራሪነት”ሲወነጅሉ ይደመጣሉ። ጉባኤውን የመሩት ...

Read More »

ቴዲ አፍሮ ለመጪው አዲስ አመት የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀርባል

ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝነኛው ኢትዮጵያዊ አቀንቃኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለመጪው 2005 የኢትዮጽያዊያን አዲስ አመት ዋዜማ ከአዲካ ኮሚውኒኬሽን ኤንድ ኢቬንትስ ጋር በመተባበር የሙዚቃ ዝግጅቱን በግዮን ሆቴል እንደሚያቀርብ ተገለፀ፡፡ በቅርቡ የወጣውን ጥቁር ሰው የተባለውን አልበሙን አስመልክቶ በሚደረገው በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከ15 ሺ በላይ የቴዲ አድናቂዎች ይታደማሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ ጥቁር ሰው ተብሎ የሚጠራው አልበሙ ለህዝብ ከቀረበ ...

Read More »

አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እየሰሩ ነው ተባለ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትና ለ19 አመታት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት አቶ ስዩም መስፍን፤ ከቻይና ተመልሰው በአዲስ አበባ ቤተመንግስት የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ፍኖተነጻነት ዘግቧል። አቶ መለስ ከተሰወሩ ጀምሮ “እረፍት ላይ ናቸው፤ ሕክምና እየተከታተሉ ነው፤ አሁንም አመራር የሚሰጡት እሳቸው ናቸው፤ ከሳምንት በሁዋላ ይመለሳሉ” የሚሉ የተለያዩ መግለጫዎች በመንግስት የተሰጡ ሲሆን፤ ኢሳት አቶ መለስ ...

Read More »

የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ተስማሙ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አስራ አንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበረሰባት የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን ለዴሞክራሲያዊ ስርእት ግንባታ ለማብቃት እንዲቻል በጋራ የተደራጀ ትግል ለማድረግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ድርጅቶቹ ትናንት ነሀሴ አንድ ቀን ባወጡትና ባሰራጩት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የትብብራቸውና የጋራ ትግላቸው ዓላማ በኢትዮጵያ አንድነት ስር አስተማናኝና፤ በህዝብ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መመስረት ነው። በመግለጫው መሰረት ...

Read More »

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል አሉ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ሊቀመንበርና የመድረክ ም/ሊ/መ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህንን የተናገሩት፤ ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ኢህአዴግ የመንግስት አመራር ለሕዝብ ግልጥ በሆነ መንገድ መከናወን አንዳለበት የሕገመንግስ አንቀጽ 12 ደንግጓል። በተጨማሪም ማንኛውም የሕዝብ ተመራጭ ሀላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ተጠያቂ እንደሚሆን አስፍሯልና ኢህአዴግ ይሄንን ባለማድረጉ ሕዝብ አመኔታ ስላጣ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት ብለዋል፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ። ...

Read More »

አርቲክል 19 አዋጅ ቁጥር 761/2004ን ተቃወመ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱን በለንደን ያደፈረገውና አርቲክል 19 በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያሳለፈውን አዋጅ ቁጥር 761/2004፤ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት የሚገድብ አፋኝ ሕግ መነሆኑን ገለጸ። አርቲክል 19 ሕጉን በመተንተን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፤ “የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ማጭበርበርን ለመከላከል” በሚል ሽፋን፤ የጸረ-ሽብር ህጉን ማጠናከሪያና፤ መንግስት በአገልግሎቱ ዘርፍ የያዘውን ሞኖፖሊ ለማስጠበቅ የወጣ ነው ሲል ተችቷል። አርቲክል 19፤ የኢትዮጵያ ...

Read More »

ጋዜጠኛዋ በምሽት በደህንነቶች ተጠለፈች

ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን በሽብርተኝነት ለመክሰስ የወሰነው የኢህአዴግ መንግስት፤ አንዲት ጋዜጠኛን በምሽት  በደህንነቶች በማስጠለፍ  በተመስገን ላይ በሀሰት እንድትመሰክር  ትዕዛዝ እና ማስፈራሪያ መስጠቱን የማዕከላዊ ምንጮቻችን አጋለጡ። ምንጮቻችን እንዳሉት፤  በአንድ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ የምትሠራ ጋዜጠኛ  ባለፈው ሐሙስ ምሽት ከቢሮዋ ወጥታ በኮንትራት ታክሲ ወደ ቤቷ በምታመራበት ወቅት  የደህንነት ሀይሎች ታክሲዋን አግተው በመጥለፍ ወደ ማዕከላዊ ...

Read More »

አቶ ጁነዲን ከሥልጣናቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ እነ ሚሚ ስብሀቱ ጠየቁ

ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን  ከሃላፊነታቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ እነሚሚ ስብሀቱ  መንግስትን አሣሰቡ። “ዛሚ ኤፍ.ኤም “ ተብሎ በሚጠራው  የነሚሚ ስብሀቱ ራዲዮ ጣቢያ በየሳምንቱ አርብ  በሚተላለፈው የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ የተሰኘ ፕሮግራም ላይ መደበኛ ተወያይ የሆኑት የኢቲቪዎቹ መሰረት አታላይ እና ሳሙኤል ፍቅሬ፣ የኢትዮጵያ ፈርስት ድረ-ገጽ አዘጋጅ  ቤን ፣የቀድሞ የኢነጋማ ጸሀፊ የነበረውና  ከማህበሩ ተለያቶ  ወደ መንግስት ...

Read More »

ሄላሪ ክሊንተን “ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ

ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሄላሪ ክሊንተን በሰሞኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ፦_“ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ። ሰሞኑን ወደ ሰባት የ አፍሪቃ አገሮች ጉዞ ያደረጉት ሄላሪ ክሊንተን በሴኔጋሉ ጉብኝታቸው ባደረጉት ንግግር  የ አፍሪቃ አገሮች ለዲሞክራሲ እና ለ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መረጋገጥ ከመስራት ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው  በማሣሰብ፤ሌላ አጋር ፍለጋ  ባልሆነ መንገድ እየሄዱ ያሉት ከዚህ ...

Read More »