የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ተስማሙ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አስራ አንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበረሰባት የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን ለዴሞክራሲያዊ ስርእት ግንባታ ለማብቃት እንዲቻል በጋራ የተደራጀ ትግል ለማድረግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

ድርጅቶቹ ትናንት ነሀሴ አንድ ቀን ባወጡትና ባሰራጩት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የትብብራቸውና የጋራ ትግላቸው ዓላማ በኢትዮጵያ አንድነት ስር አስተማናኝና፤ በህዝብ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መመስረት ነው።

በመግለጫው መሰረት ሁሉንም የዴሞክራሲ ሀይሎች የሚያሳትፍ የሽግግር ሂደት እንዲኖር ለማስቻል፤ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ በሚረቀቅ ሕገመንግስት፤ ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተናግድ ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ስርአት እንዲሰፍን እንታገላለን ብለዋል፤ በጋራ ለመስራት የተስማሙት 11 ድርጅቶች።

ይህንን ሂደት በአግባቡ መከናወኑን የሚከታተል የመረጃ ልውውጥና የድርጅቶችን ግንኙነት የሚያቀላጥፍ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ካሉት ከሁሉም ተሳታፊ ድርጅቶች የተወጣጡ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፤ እንደሚዋቀሩ ድርጅቶቹ ባወጡት በዚህ መግለጫ ገልጠዋል።

በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊና ፍትሀዊ ስርአት እውን እንዲሆን፤ እንዲሁም ሀገሪቱ ካለችበት ቀውስ እንድትወጣ ለማስቻል በሚደረገው ትግል፤ ሁሉም ድርጅቶችና አጠቃላይ የኢትዮጵ ህዝቦች ከጎናቸው አንዲቆሙ ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አድርገዋል።

በዚህ መሰረት የአገሪቱ የጦር ሰራዊት የስራ ድርሻ አንድነ ግለሰብ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ማገልገል ሳይሆን የአገሪቱን አንድነትና ሉአላዊነትና እንዲሁም የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን ተገንዝቦ፤ ከህዝብ ን እንዲቆም ድርጅቶቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide