አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እየሰሩ ነው ተባለ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትና ለ19 አመታት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት አቶ ስዩም መስፍን፤ ከቻይና ተመልሰው በአዲስ አበባ ቤተመንግስት የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ፍኖተነጻነት ዘግቧል።

አቶ መለስ ከተሰወሩ ጀምሮ “እረፍት ላይ ናቸው፤ ሕክምና እየተከታተሉ ነው፤ አሁንም አመራር የሚሰጡት እሳቸው ናቸው፤ ከሳምንት በሁዋላ ይመለሳሉ” የሚሉ የተለያዩ መግለጫዎች በመንግስት የተሰጡ ሲሆን፤ ኢሳት አቶ መለስ እንደሞቱ ከአይ ሲ ጂ ከተገኙ  ምንጮች ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

አቶ መለስ ስላሉበት ሁኔታ ግን መንግስት በምስልም ሆነ በድምጽ የታጀበ ማስተባበያ እስካሁን አላቀረበም።

_____________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide