ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ይጠበቅበታል አሉ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአንድነት ሊቀመንበርና የመድረክ ም/ሊ/መ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህንን የተናገሩት፤ ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።

ኢህአዴግ የመንግስት አመራር ለሕዝብ ግልጥ በሆነ መንገድ መከናወን አንዳለበት የሕገመንግስ አንቀጽ 12 ደንግጓል። በተጨማሪም ማንኛውም የሕዝብ ተመራጭ ሀላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ተጠያቂ እንደሚሆን አስፍሯልና ኢህአዴግ ይሄንን ባለማድረጉ ሕዝብ አመኔታ ስላጣ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት ብለዋል፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እግራቸው ላይ ባጋጠማቸው ሕመም በጀርመን አገር ሲታከሙ ቆይተው፤ አዲስ አበባ የገቡት ከ2 ሳምንት በፊት መሆኑ ይታወቃል።

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide