አርቲክል 19 አዋጅ ቁጥር 761/2004ን ተቃወመ

ነሀሴ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱን በለንደን ያደፈረገውና አርቲክል 19 በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያሳለፈውን አዋጅ ቁጥር 761/2004፤ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት የሚገድብ አፋኝ ሕግ መነሆኑን ገለጸ።

አርቲክል 19 ሕጉን በመተንተን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፤ “የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ማጭበርበርን ለመከላከል” በሚል ሽፋን፤ የጸረ-ሽብር ህጉን ማጠናከሪያና፤ መንግስት በአገልግሎቱ ዘርፍ የያዘውን ሞኖፖሊ ለማስጠበቅ የወጣ ነው ሲል ተችቷል።

አርቲክል 19፤ የኢትዮጵያ መንግስት ህጉን ሙሉ በሙሉ እንዲሽር፤ የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍን እንዲያሻሽል፤ እንዲሁም የጸረሽብር ህጉ፤ የቴሌኮሙኒኬሽንን ዘርፍም ለመገደብ ስራ ላይ ሊውል አይገባም ብሏል።

አክሎም የኢትዮጵያዊያን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በየትኛውም ህግ ሊገደብ አይገባም ሲል ድርጅቱ አስገንዝቧል።

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide