ሄላሪ ክሊንተን “ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ

ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሄላሪ ክሊንተን በሰሞኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ፦_“ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ።
ሰሞኑን ወደ ሰባት የ አፍሪቃ አገሮች ጉዞ ያደረጉት ሄላሪ ክሊንተን በሴኔጋሉ ጉብኝታቸው ባደረጉት ንግግር  የ አፍሪቃ አገሮች ለዲሞክራሲ እና ለ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መረጋገጥ ከመስራት ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው  በማሣሰብ፤ሌላ አጋር ፍለጋ  ባልሆነ መንገድ እየሄዱ ያሉት ከዚህ ተጠያቂነትለማምለጥ  እንደሆነ በማብራራት ወቅሰዋል።

ክሊንተን በዚሁ ጉብኝታቸው ቻይና በኢንቨስትመንት ስም   የአፍሪቃን ሀብት በስፋት እየዘረፈች እንደሆነም የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል።

<ዡንዋ> የተሸኘው የቻይና ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፤ሒላሪ ክሊንተን በአፍሪካ  አገሮች እያደረጉ  ባሉት ጉብኝት ቻይናን አስመልክቶ ያደረጉት ንግግር ፤ የቻይና መንግስትን አስቆጥቷል።

“ሒላሪ ክሊንተን ስለአፍሪካ ዕውነታ ባዕድ  ናቸው፤ አለያም  ላለማወቅ ሆነ ብለው  ጆሮሯቸውን ደፍነዋል” ያለው  የቻይና መንግስት፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ንግግር በቻይና እና በአፍሪቃ ግንኙነት መካከል ክፍተት በመፍጠር የአሜሪካን  ጥቅም ለማራመድ ካለመ  ራስ ወዳድነት የመነጨ ነው” ብሏል።

የሄላሪ ክሊንተንን ንግግር፦” እውነታን ያላገናዘ፣ ተራ እና  ስውር አጀንዳ ያለው” በማለት ያጣጣለው  የቻይና መንግስት፤  ቻይና አፍሪካ ውስጥ ለልማትና ለኢንቨስትመንት  ቢሊዮን  ዶላሮች ማፍሰሷንና  የአፍሪካ ዋነኛ አጋር መሆኗን  ጠቅሷል::

ሂላሪ ክሊንተን በቻይና ላይ የዚህ ዓይነት ወቀሳ ሢሰነዝሩ የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።

ከዓመት በፊት በተመሠሳይ በአፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት፤ ቻይና በኢንቨስትመንት ስም  የአፍሪካን ሀብት እና ርካሽ ጉልበት  እየበዘበዘች እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

_____________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide