ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በኩዌት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እራሷን አጠፋች

ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አረብ ታይምስ ትናንት ባወጣው ዘገባ እንደገለፀው ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊቷ ትሰራበት የነበረው ቤት ውስጥ ራሷን የመግደል ሙከራ ስታደርግ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ስነልቦና ሕክምና እንድትወስድ ተደርጋ ነበር። ሆኖም ከሆስፒታሉ ስትወጣ  “ጃሃራ” በሚባል ስፍራ ወደሚገኘው “አል-ነኢም” ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ በመታሰር በምርመራ ላይ ሳለች፤ የእስር ቤቱ መታጠቢያ ቤት ውስጥ አድርጋው በነበረው ሂጃብ  የራሷን ሕይወት አጥፍታ ተረኛው ፖሊስ እስረኞችን በሚጎበኝበት ወቅት አስከሬኗን ማግኘቱን ዘግቧል።

አረብ ታይምስ ሟቿ ኢትዮጵያዊ መሆኗን ከመግለጽ በቀር ስለማንነቷ የገለፀው ምንም አይነት መረጃ የለም።

_____________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide