ክረምቱ ሲገባ የአረቡ አብዮት ወጀብ ወደ ኢትዮጵያ እየነፈሰ ነው ሲል ረዩተርስ ዘገበ

ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የረዩተርሱ ጆን ሊዮልድ ባቀረበው ሰፊ ዘገባ በአረቡ አለም የተጀመረው ህዝባዊ ማእበል ፣ ወደ ጥንታዊቷ የስልጣኔ ማእከል ፣ ኢትዮጵያም፣  እየገሰገሰ ነው። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ መለስ ዜናዊ ካለፈው የሰኔ ወር ጀምሮ ተቃዋሚዎችን፣  ጋዜጠኞችን እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላትን ማዋከብ ፣ ማሰርና አገር ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጋቸውን ረዩተርስ ገልጣዐል። በቅርቡ የስደትን ጎራ ከተቀላቀሉት መካከል የሲፒጄ የነጻነት ተሸላሚ የአውራምባ ...

Read More »

የፌዴራል ፖሊስ መርማሪዎች በፖለቲካ እሥረኞች ላይ የማሰቃያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ምንጮቻችን አስታወቁ

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪዎች በፖለቲካ እሥረኞች ላይ የተለያዩ የማሰቃያ ወይም የቶርቸር ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ምንጮቻችን አስታወቁ፡ ለታሳሪዎች ከቤተሰብ የሚመጣውን የዘወትር ምግብ ደግሞ በአብዛኛው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ለእራሳቸው እንደሚመገቡት ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ወዲህ በከተሞችና በክልሎች አካባቢ በሚነሱ የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት፣  የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጥያቄዎች የደህንነት ሠራተኞችና የፌዴራል መንግሥት ፖሊሶች  በቁጥጥር ...

Read More »

ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደመወዛችን አይቆረጥብንም ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ” ጸረ-ሰላም ሀይሎች ” የሚል ደብዳቤ እየደረሳቸው ነው

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደመወዛችን አይቆረጥብንም ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ” ጸረ-ሰላም ሀይሎች ” የሚል ደብዳቤ እየደረሳቸው ነው። የተለያዩ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ለኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጡት፣ የኢትዮጵያ የሰራተኛ አሰሪ አዋጅ አንድ ሰው ደመወዙን ያለራሱ ፈቃድ  ወይም ያለፍድር ቤት ትእዛዝ እንደማይቆረጥበት ተደንግጎ ቢገኝም፣ መንግስት ግን ከሰራተኞች ላይ በግዳጅ እንዲቆረጠ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ...

Read More »

መንግስት በአህባሽ የእስልምና አስተምህሮ ያሰለጠናቸውን 300 ሰዎች አስመረቀ

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በታጠቅ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአህባሽ የእስልምና አስተምህሮ ላይ ስልጣና የወሰዱት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ የሚታየውን የእስልምና አክራሪነት እንዲዋጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ስልጠናው በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም፣  በአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ በኮማንደር መኮንን አሻግሬ እና የአህባሽን አስተምህሮ በሚከተሉ ሙስሊሞች አማካኝነት መሰጠቱ ታውቋል። ለሰልጣኞቹ የተሰጠው ስልጠና በዋነኝነት ያተኮረው ፣ አህባሽ የተባለው የእስልምና እምነት አገርበቀል በመሆኑ ማንኛውም ...

Read More »

የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ በሁለቱ አገሮች ውጥረቱ ጨመሯል

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ  በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውጥረት መጨመሩ ታወቀ ደብረብርሀን ብሎግ  የጦር መሳሪያና ሰራዊት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜን አዲስ አበባ በኩል ሲጓዙ እንደነበር ዘግቧል። ኢሳት ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል በመደወል እንዳረጋገጠው ከሆነ እረቡ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚመሩ ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ በርካታ አውቶብሶች ወደ ሰሜን ተጉዘዋል። በድንበር ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ በዋሽንግተን ዲሲ ዝግጅት ያቀርባሉ

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ “ለመብት ተማጓቾች ይጻፉ” በሚል ርእስ በዋሽንግተን ዲሲ ናሽናል ፕሬስ ክለብ አንድ ዝግጅት  ያቀርባሉ። ዲሰምበር 9፣ 2011 በሚቀርበው ዝግጅት  ላይ የቀድሞ የአንድነት ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በክብር እንግድነት ይገኛሉ። ከ6፡30 እስከ 9፡30 በሚቆየው ዝግጅት ኢትዮጵያኖች ተገኝተው በእስር ላይ ለሚገኙት የነጻነት ታጋዮች ደብዳቤ እንዲጽፉ የአንድነት ዲሲ ሜትሮ የድጋፍ ቅርንጫፍ ...

Read More »

በ2002 ዓም ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ ፣ መንግስት በተመሳሳይ አመት መድቦት ከነበረው ገንዘብ ጋር እኩል መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ2002 ዓም ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ ፣ መንግስት በተመሳሳይ አመት መድቦት ከነበረው ገንዘብ ጋር እኩል መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ይፋ ባደረገው ቅድመ ጥናት መሰረት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2002 እስከ 2009 ባሉት 7 አመታት ውስጥ፣ ከ187 ቢሊዮን ብር ወይም 11 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገንዘብ ተዘርፎ በውጭ አገር ባንኮች ተቀምጧል። ...

Read More »

ህወሀት፤ የድርጅቱን ታሪክ በአዲስ መልክ ለማፃፍ 43 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተጠቆመ

ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ “ከአገር በስተጀርባ”  መጽሐፍ  ደራሲን በመጥቀስ ፍኖተ-ነፃነት እንዳስነበበው፤የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ዶክተር ሰሎሞን ዕንቋይን “ጠልመት” እና የ አቶ ሀይላይ ሀድጉ ሥራ የሆነውን “ንንዓት” የተባሉትን መጽሀፍት መሰረት በማድረግ፤ የህወሀትን ታሪክ በአዲስ መልክ  በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለማፃፍ 43 ሚሊዮን ብር ተመድቧል። “የሀብት ብዛትና ስልጣን እውነተኛውን ታሪክ ሊቀይሩት አይችሉም” ያሉት የመጽሐፉ ደራሲ፤ “43 ሚሊዮን ብር ቀርቶ 43 ...

Read More »

የስዊድን ጋዜጠኖች የመለስ መንግስት ያቀረበውን የሽብርተኝነት ክስ ፈጠራ ነው አሉ

  ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኞቹ ማክሰኛ እለት በዋለው ችሎት እንደገለጡት ፣ ወደ ኦጋዴን ክልል የገቡት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅትን ለመርዳት ሳይሆን በአካባቢው በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ሉንዲን ኦይል የተባለውን  የስዊዲሽ የነዳጅ ኩባንያ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሰሰውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት አባላት በዘበኝነት መቅጠሩን ለማረጋገጥ ነው።  ጋዜጠኛ ማርቲን ሺቢዬና ጆሀን ፔርሰን እንዳሉት ከኦብነግ ጋር የነበራቸው ግንኙነት የጋዜጠኝነት ስነምግባርን በተከተለ ...

Read More »

በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር የወጣው ገንዘብ 11 ቢሊዮን ደረሰ፣ ኢትዮጵያውያን እየደሙ ነው

ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስርቆት፣ በሙስናና በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች  ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር የወጣው ገንዘብ 11 ቢሊዮን መድረሱን አንድ ታዋቂ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ፣ ኢትዮጵያውያን እየደሙ ነው ሲል የድርጊቱን አስከፊነትም ገልጧል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት መርሀግብር ወይም ዩኤን ዲ ፒ የገንዘብ ድጋፍ ጥናቱን ያካሄደው “ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው የቅድመ ዳሰሳ ሪፖርት ፣ እጅግ ደሀ ከሆነችው ኢትዮጵያ ...

Read More »