ተመድለ6.5 ሚሊዮንኢትዮጵያውያንየምግብዕርዳታሊሰጥነው

ግንቦት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጄኔቭየተመድጽህፈትቤትየወጣውመግለጫእንደሚያመለክተውበአንበጣመንጋጥቃት፣በጐረቤትአገርጦርነትናበዝናብእጥረትምክንያትኢትዮጵያለ6 ነጥብ 5 ሚሊዮንሰዎችዕርዳታያስፈልጋታልብሏል፡፡

‹‹የአንበጣመንጋወረራበምሥራቅየአገሪቱክፍልመከሰቱአሳስቦናል>> ያሉትየዓለምምግብፕሮግራምቃልአቀባይኤልዛቤትባይርስ፤ <<ይህበአግባቡካልተያዘለአርብቶአደሩማኅበረሰብበጣምአሳሳቢነው፤›› ሲሉተናግረዋል።

በሰሜንኢትዮጵያአካባቢዎችየዝናብሥርጭቱከአማካዩጋርሲነፃፀርባለፉትሦስትናአራትዓመታትእየቀነሰመምጣቱንቃልአቀባይዋአመልክተዋል፡፡በመሆኑምለችግርየተጋለጡትበአካባቢውያሉነዋሪዎችዕርዳታማግኘትእንዳለባቸውገልጸዋል።

ሟቹጠቅላይሚኒስትርአቶመለስዜናዊበስልጣንማግስትየኢትዮጵያህዝብበቀንሦስትጊዜሲበላየማየየትምኞትእንዳላቸውየገለፁቢሆንም፤ከሀያሦስትየአገዛዝዓመታትበሁዋላሀገሪቱከምግብእህልእርዳታ አሁንምልትላቀቅአለመቻሉዋን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከተፈጥሮአዊችግሮችበተጨማሪበደቡብሱዳንበተፈጠረውግጭትምክንያትበርካታስደተኞችወደኢትዮጵያበመፍለሳቸውእናይህምበኢትዮጵያየስደተኞችቁጥርእንዲጨምርበማድረጉ፣የዓለምየምግብፕሮግራምበጀትመዛባቱንቃልአቀባይዋጠቁመዋል፡፡

ባለፉትስድስትወራትከ120 ሺሕበላይየደቡብሱዳንስደተኞችድንበርተሻግረውኢትዮጵያመግባታቸውንያመለከተውየተመድመግለጫ፤ ከስደተኞቹመካከልበርካታሴቶችናሕፃናትመጐዳታቸውንአመልክቷል፡፡

በአገሪቱየስደተኞችጠቅላላቁጥርወደ 500 ሺማሻቀቡንየጠቀሰውተመድ፤ይኸምበኢትዮጵያላይተጨማሪጫናስለሚያሳድርድርጅቱየምግብዕርዳታለማቅረብመገደዱንአስታውቋል፡፡