ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፕሬዚዳንት ኦባማ ለኢትዮጵያ ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ

ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ኦባማ ለዲሞክራቲክ ፓርቲያቸው ገንዘብ ለማሰባሰብ በተገኙበት አንድ ስብሰባ ላይ ነው፣ አበበ ንግግራቸውን አቋርጦ ስለኢትዮጵያ ነጻነት ጥያቄ ያቀረበው።

ጋዜጠኛ አበበ ” ፕሬዚዳንት ኦባማ እንወድዎታለን፣ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ነጻነት እንፈልጋለን” ሲል በንግግራቸው ጣልቃ ገብቶ መልእክቱን አስተላልፏል።

“ሰምቼሃለሁ፣ ንግግሬን ልጨርስና በሁዋላ እንወያያለን” በማለት ፕሬዚዳንቱ ቢመልሱም፣ አበበ ንግግሩን በመቀጠል  ” ኦባማ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ይቁሙ” ብሎአቸዋል።

ፕሬዚዳንት አባማ ንግግራቸውን እያጠቃለሉ በነበረበት ሰአት እንዳቋረጣቸው በመግለጽ፣ ይሄ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የሚቻልበት አገር ነው በማለት ንግግራቸውን ቀጥለዋል።

ጋዜጠኛ አበበ ከሁለት አመት በፊት አቶ መለስ አሜሪካ ውስጥ ተጋብዘው ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ  ጋዜጠኛ አበበ ተቃውሞአቸው እንደነበር ይታወቃል።

አበበ በድጋሜ በድፍረት ያነሳው የነፃነት ጥያቄ  የማህበራዊ ሚዲያዎችን ትኩረት መሳቡም ታውቋል።

አቶ መለስ በድንጋጤ የአበበን ተቃውሞ ካስተናገዱ ከጥቂት ወራት በሁዋላ መሞታቸው ይታወሳል።