የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ታዘዙ

ግንቦት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ዩኒቨርስቲው ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ አንዳንድ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት መጀመራቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች እንደገለጹት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወደ ዘመዶቻቸው የተመለሱ በመሆኑ በግቢው ውስጥ የሚታዩት ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው።

ተማሪዎች እንደሚሉት በግቢው ውስጥ የሚታየው ሁኔታ አሁንም አስፈሪ ነው። ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ ያልቻሉና በቤተክርስቲያናትና በአካባቢው ሰዎች መኖሪያ ቤቶች ተጠግተው የቆዩ ተማሪዎች ከችግር ብዛት ወደ ዩኒቨርስቲው ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ከ40 በላይ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች አሁንም አለመፈታታቸው ታውቋል።