በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሪታንያ መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ትኩረት ሰጥታ እንደትከታተለው የሚያሳስቡ የተቃውሞ ሰልፎች ካለፈው ወር ጀምሮ በእየሳምንቱ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ዛሬ አርብም ለአምስተኛ ጊዜ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን በከፍተኛ ቁጣ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው ያነጋገርነው ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹ ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ግብረሃይል በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳምንት ለአንድ ሰአት ...

Read More »

የኢህአዴግ ተወካዮች ምሬታቸውን ገለጹ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ  የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ችግር እንዳለም ገልጸዋል። ...

Read More »

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ሁለት ኢትዮጵያውያን ዩጋንዳ ውስጥ ተያዙ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኒው ቪዥን እንደዘገበው አበበ መኮንንና አስፋው ወንዶሰን ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው ተወስደዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹንለመያዝ ለሁለት ቀናት አሰሳ ሲያካሂድ እንደነበር ተዘግባል። ኢትዮጵያውያኑ ለኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ተላልፈው ይሰጡ ወይም ጉዳያቸው በዩጋንዳ ፍርድ ቤት ይታይ በዘገባው አልተጠቀሰም። ፖሊስ እስረኞቹ የታሰሩበትን ቦታም ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።

Read More »

በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ያለው ግጭት አገረሸ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሶስት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው የእስራኤልና የፍልስጤማውያን ግጭት እንደገና ማገርሸቱን እስራኤል አስታውቃለች። በግብጽ አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር ሃማስ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባ ጀምራለች። ሃማስ የሰላም ድርድሩ እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገቸውን ከበባ ማስቆም አለበት የሚል አቋም ይዟል፡፤ እስረኤል በግብጽ በመካሄድ ላይ ያለውን የሰላም ድርድር አልሳተፍም በማለት ልኡካኖቿን አስወጥታለች። ከ1900 ...

Read More »

የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት7 የኦህዴድ ደግሞ ከኦነግ ጋር እያበሩ ነው ሲል አቶ አዲሱ ለገሰ ያዘጋጁትና ለጠ/ሚ አማካሪዎች የተላከው ሰነድ አመለከተ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ እንዲሁም በጋምቤላ ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል። በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል። የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ  ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት ማንኮላሻ አቅም ግንባታ እና የአመራር ...

Read More »

ወጣቱ ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እስር ቤት ውስጥ እንደተደበደበ ለፍርድ ቤት ተናገረ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመቀሌ በሚጽፋው ጽሁፎችና በሚሰጣቸው አስተያየቶች የበርካታ ወጣቶችን ቀልብ የሳበው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብርሃ ደስታ፣ በአሸባሪነት ተከሶ መእከላዊ እስር ቤት ከገባ በሁዋላ ፖሊስ ፍድር ቤት  ያቀረበው ሲሆን፣ አብርሃ በፖሊሶች መደብደቡን፣ እርሱ ያልጻፋቸውን ጽሁፎች የራሱ ጽሁፎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲፈርም መገደዱን፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻውን እንዲቀመጥ መደረጉን እንዲሁም ፖሊሶች ያልሆኑ ሰዎች ምርምራ እንደሚያካሂዱበት ተናግሯል። በውጭ ከሚጠባበቁ አድናቂዎችና ...

Read More »

መኢአድና አንድነት ህዝቡ ለትግል እንዲነሳ ጥሪ አቀረቡ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመላውኢትዮጵያአንድነትድርጅት (መኢአድ) እናከአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጋራ ባወጡት መግለጫ  “በህውሓት/ኢህአዴግአባላትየሚመራውየኢትዮጵያምርጫቦርድበሰላማዊትግሉላይከፍተኛ መሰናክሎችንበመፍጠርከዚህቀደምየተደረጉምርጫዎች እንዲቀሙ፣እንዲዘረፉናኮሮጆእየተገለበጠለገዢውፓርቲእንዲሰጥከፍተኛሚናሲጫወትመቆየቱ”አንሶ ፣ “ዛሬበግልጽፓርቲዎችንለመዝጋትመሞከሩ በኢትዮጵያሕዝብላይእየፈፀመውያለውከድፍረቶችሁሉድፍረትነው ” ብሎአል፡፡ ” የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድከዚህአድራጐቱተቆጥቦትክክለኛየሆነየምርጫሜዳየማያዘጋጅከሆነበሰላማዊሰልፍናማንኛውንምየሰላማዊትግልስልቶችን ሁሉበመጠቀምየምንታገልመሆኑንእናሳውቃለን፡፡” የሚለው መግለጫው፣  ይህንስናደርግሊያስሩን፣ሊያሳድዱንናሊገድሉንእንደሚሞክሩብናውቅም፣በሕዝባችን ላይእየደረሰካለውመከራናየሰቆቃኑሮስለማይብስየሚደርስብንንሁሉለ መሸከምዝግጁዎችስንሆንሕዝባችንምከጐናችንእንደሚቆምበመተማመንነው፡፡ ” ብለዋል። ወጣቱናአዛውንቱበሚደረገውማንኛውምየሰላማዊትግልእንቅስቃሴሁሉ፣በተግባርከጐናቸው እንዲቆም፣በእድሜየገፉአባቶችናእናቶችደግሞበፀሎታቸው እንዲያግዙ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል። ምርጫ ቦርድ ውህደትለመፈፀምያጠናቀቁትንመኢአድናአንደነትንየተለያዩመሰናክሎችንእንዳይዋሃዱ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑንም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብሁኔታውንበጥሞናናበእርጋታበመከታተልየዜጎችንመብትለማስከበርበሚደረገውጥረትሁሉከታጋዩችጐንእንዲቆም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል። ለደህንነት፣የፖሊስ  እናየመከላከያሠራዊቱአባላት ባቀረቡት ጥሪ ደግሞ ” ጥቂቶቹንበሥልጣንላይለማቆየትአንተመሰቃየትናመሞትየለብህም፡፡ጥቂቶቹጠንካራየፖለቲካፓርቲዎችንበማጥፋትበሥልጣንላይለመቆየትበሚደረገውአድማናሴራየተነሳዜጎችለመብታቸውመከበርሲንቀሳቀሱ አንተዜጎችንማሰቃየትናመግደልየለብህም ፣አንተምበተመሳሳይሁኔታለማይጠቅምነገርመሰዋዕትመሆንየለብህም፡፡ስለዚህየመንግሥትሥልጣንዲሞክራሲያዊናሰላማዊበሆነመንገድመሸጋገርይችል ዘንድበምናደርገው ...

Read More »

ክስ የተመሰረተባቸው መጽሄቶች ከእንግዲህ ላይታተሙ ይችላሉ ተባለ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ሕገመንግሥቱንናሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበኃይልለመናድናሕዝቡበመንግሥትላይ አመኔታእንዲያጣአድርገዋል በሚልመከሰሳቸውንበመንግሥትመገናኛብዙሃንባለፈውማክሰኞእለትየሰሙትአምስትመጽሔቶችእናአንድጋዜጣ ከእንግዲህሊታተሙእንደማይችሉከወዲሁምልክቶችበመታየትላይናቸው። በተለይአዲስጉዳይ፣ፋክትእናሎሚመጽሄቶችአሳታሚዎችእስካሁንበመንግሥትመገናኛብዙሃንከሰሙትዜናውጪ በይፋየደረሳቸውክስየሌለሲሆን ነገርግንመንግሥትባሰራጨውፕሮፖጋንዳምክንያትበተለይየህትመትድርጅቶች ፕሬሶቹንላለማተምእያንገራገሩመሆኑታውቋል፡፡በዚህምክንያት የፊታችንቅዳሜዕለትመውጣትየነበረበት አዲስጉዳይመጽሔትበዕለቱየማይወጣመሆኑከወዲሁየተረጋገጠሲሆንየፋክትእናየሎሚመጽሔቶችምየመውጣት፣ ያለመውጣታቸውነገርባይለይለትም ያለመውጣታቸውጉዳይግንያመዘነመሆኑታውቋል፡፡ የብሮድካስትባለስልጣንበሰኔወር 2006 ባወጣውመረጃመሰረትፋክትበወርበአማካይ 17 ሺ 993፣አዲስጉዳይ በወር 11 ሺ 750፣ሎሚበወር 11 ሺ 250 የኮፒብዛትወይንም  ከፍተኛስርጭትያላቸውመጽሔቶችመሆናቸውን አስታውቆአል፡፡

Read More »

የደቡብ ሱዳን አማጽያን በአዲስ አበባ ሊካሄድ በነበረው ድርድር ላይ ሳይገኙ ቀሩ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አማጽያኑ በአዲስ አበባው ጉባኤ ላይ ለመገኘት ለምን እንዳልፈቀዱ ግልጽ አይደለም። ይህ አቋማቸው ያአበሳጫቸው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻርን ተጠያቂ አድርገዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ ሁለቱም ሃይሎች ወደ ሰላም ስምምነቱ የማይመጡ ከሆነ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች እርምጃ ይወስዳሉ ብለዋል። በደቡብ ሱዳን አሁንም ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እልቂት እየደረሰ ነው፡፡ ሁለቱ ሃይሎች ቀደም ...

Read More »

የአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞኑ ፖሊሶች ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አመራሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ ፍተሻ ካደረጉ በሁዋላ ፣ አመራሮችን ወስደው አስረዋቸዋል። የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘናል በማለት ፍተሻ ያካሄዱት ፖሊሶች በአንደኛው ቤት ውስጥ ሁለት ፍሬ ጥይቶችን ማግኘታቸውን ሲያስታወቁ፣ በሌሎች መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ቪዲዮ ካሜራዎችን፣ ፊልሞችንና የተለያዩ ወረቀቶችን ሰብስበው ወስደዋል። የአንደኛው አመራር የቅርብ ሰው ...

Read More »