በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ሁለት ኢትዮጵያውያን ዩጋንዳ ውስጥ ተያዙ

ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኒው ቪዥን እንደዘገበው አበበ መኮንንና አስፋው ወንዶሰን ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው ተወስደዋል። ፖሊስ

ተጠርጣሪዎቹንለመያዝ ለሁለት ቀናት አሰሳ ሲያካሂድ እንደነበር ተዘግባል።

ኢትዮጵያውያኑ ለኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ተላልፈው ይሰጡ ወይም ጉዳያቸው በዩጋንዳ ፍርድ ቤት ይታይ በዘገባው አልተጠቀሰም። ፖሊስ እስረኞቹ የታሰሩበትን

ቦታም ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።