የደቡብ ሱዳን አማጽያን በአዲስ አበባ ሊካሄድ በነበረው ድርድር ላይ ሳይገኙ ቀሩ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አማጽያኑ በአዲስ አበባው ጉባኤ ላይ ለመገኘት ለምን እንዳልፈቀዱ ግልጽ አይደለም። ይህ አቋማቸው ያአበሳጫቸው

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻርን ተጠያቂ አድርገዋል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ ሁለቱም ሃይሎች ወደ ሰላም ስምምነቱ የማይመጡ ከሆነ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች እርምጃ ይወስዳሉ ብለዋል።

በደቡብ ሱዳን አሁንም ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እልቂት እየደረሰ ነው፡፡ ሁለቱ ሃይሎች ቀደም ብሎ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በመጣስ እየተዋጉ መሆኑን

ዘገባዎች ያመልክታሉ።