መኢአድና አንድነት ህዝቡ ለትግል እንዲነሳ ጥሪ አቀረቡ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመላውኢትዮጵያአንድነትድርጅት (መኢአድ) እናከአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህ

ፓርቲ (አንድነት) በጋራ ባወጡት መግለጫ  “በህውሓት/ኢህአዴግአባላትየሚመራውየኢትዮጵያምርጫቦርድበሰላማዊትግሉላይከፍተኛ

መሰናክሎችንበመፍጠርከዚህቀደምየተደረጉምርጫዎች

እንዲቀሙ፣እንዲዘረፉናኮሮጆእየተገለበጠለገዢውፓርቲእንዲሰጥከፍተኛሚናሲጫወትመቆየቱ”አንሶ ፣ “ዛሬበግልጽፓርቲዎችንለመዝጋትመሞከሩ

በኢትዮጵያሕዝብላይእየፈፀመውያለውከድፍረቶችሁሉድፍረትነው ” ብሎአል፡፡

” የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድከዚህአድራጐቱተቆጥቦትክክለኛየሆነየምርጫሜዳየማያዘጋጅከሆነበሰላማዊሰልፍናማንኛውንምየሰላማዊትግልስልቶችን

ሁሉበመጠቀምየምንታገልመሆኑንእናሳውቃለን፡፡” የሚለው መግለጫው፣  ይህንስናደርግሊያስሩን፣ሊያሳድዱንናሊገድሉንእንደሚሞክሩብናውቅም፣በሕዝባችን

ላይእየደረሰካለውመከራናየሰቆቃኑሮስለማይብስየሚደርስብንንሁሉለ

መሸከምዝግጁዎችስንሆንሕዝባችንምከጐናችንእንደሚቆምበመተማመንነው፡፡ ” ብለዋል።

ወጣቱናአዛውንቱበሚደረገውማንኛውምየሰላማዊትግልእንቅስቃሴሁሉ፣በተግባርከጐናቸው እንዲቆም፣በእድሜየገፉአባቶችናእናቶችደግሞበፀሎታቸው

እንዲያግዙ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ምርጫ ቦርድ ውህደትለመፈፀምያጠናቀቁትንመኢአድናአንደነትንየተለያዩመሰናክሎችንእንዳይዋሃዱ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑንም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብሁኔታውንበጥሞናናበእርጋታበመከታተልየዜጎችንመብትለማስከበርበሚደረገውጥረትሁሉከታጋዩችጐንእንዲቆም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

ለደህንነት፣የፖሊስ  እናየመከላከያሠራዊቱአባላት ባቀረቡት ጥሪ ደግሞ ” ጥቂቶቹንበሥልጣንላይለማቆየትአንተመሰቃየትናመሞትየለብህም፡፡ጥቂቶቹጠንካራየፖለቲካፓርቲዎችንበማጥፋትበሥልጣንላይለመቆየትበሚደረገውአድማናሴራየተነሳዜጎችለመብታቸውመከበርሲንቀሳቀሱ

አንተዜጎችንማሰቃየትናመግደልየለብህም

፣አንተምበተመሳሳይሁኔታለማይጠቅምነገርመሰዋዕትመሆንየለብህም፡፡ስለዚህየመንግሥትሥልጣንዲሞክራሲያዊናሰላማዊበሆነመንገድመሸጋገርይችል

ዘንድበምናደርገው

እንቅስቃሴሁሉለመግደልሳይሆንከጎናችንለመቆምመዘጋጀትአለብህ፡፡ ” ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በመጨረሻም ” ዛሬየህውሓት/ኢህአደግመንግሥትእየጨቆነህ፣እያሳደደህ፣እያሰረህናእየገደለህያለውበዘርናበቋንቋበመከፋፈልለነፃነትህበአንድነት

እንዳትቆምበማድረግ፣የኒውኮሎኒያሊስቶችእንደሚያደርጉት

ሁሉእንደእድገትየሚቆጠርብልጭልጭየሆነናእድገትመሰልህንፃዎችንበዋናዋናመንገዶችዳርበማሳየትነው፡፡” ካሉ በሁዋላ፣   የአገርህባለቤትሳትሆንየእድገቱምባለቤትመሆንስለማትችልበአንድነትበመነሳትከዚህአስከፊየጭቆናናየብዝበዛቀንበርለመውጣትከጎናችንእንድትቆም

ጥሪያችንንእናስተላልፉለን፡፡” ብለዋል።