ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ አገሮች 33ኛ ወጣች

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ሀገራት የመልካም አስተዳደር ይዘትን የሚያጠናውና ደረጃ የሚያወጣው የ ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ባወጣው የ2012 ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ 47 ነጥብ በማግኘት 33ኛ ደረጃ መውጣቷን ይፋ አደረገ። በትውልድ ሱዳናዊ፤ በዜግነት እንግሊዘዊ በሆኑት ቢሊዮኔር ዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ይህ ተቋም፤ የአፍሪካ ሀገራትን በተለያዩ ዘርፎች በመመርመርና በማወዳደር በሰጠው ደረጃ፤ ሞሪሸስ በ83 ነጥብ የአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች። ኬፕ ቬርድና ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም በአንዋርና በበኒ መስጊዶች ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በኢህአዴግ መንግሥት ደረሰብን ላሉት የሕገ-መንግሥትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬ ከጁምዓ የጸሎት ፕሮግራም በኋላ ፒያሳ በሚገኘው የበኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡ በከፍተኛ ቁጥር ፒያሳ በሚገኘው በኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከጸሎተ ሥግደት በኋላ ለ30 ደቂቃ ያህል እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድነታቸውን ያሳዩ ...

Read More »

በአማራ ክልል ነጋዴዎች በዘፈቀደ በሚጣለው ግብር እየተማረሩ ነው

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነጋዴዎቹ በበቂ ጥናት ባልተደገፈ መልኩ በሚጣልባቸው ግብር በመማረር የንግድ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ፣ ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ጎረቤት አገሮች በተለይም ወደ ደቡብ ሱዳን በመጓዝ ላይ ናቸው ። መንግስት የአምስት አመቱን የልማት ግቦች አሳካለሁ በማለት የጀመረው እቅድ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፈተና ውስጥ እየወደቀ መምጣቱን በመመልከቱ ፣በነጋዴው ላይ ግብር ለመቆለል መገደዱን ባለሙያዎች ...

Read More »

በኢትዮጵያ ለውጭ አገር ባለሀብቶች የሚሰጡት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ዋጋ ተገቢ ነው ሲሉ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ተናገሩ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኦል አፍሪካ ዶት ኮም እንደዘገበው በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ወ/ሮ ገነት በኢትዮጵያ የጠረፍ አካባቢዎች በቂ የሆኑ የመሰረተ ልማቶች ያልተዘረጉ በመሆኑና ሰው ሀይልም በበቂ ሁኔታ አለመገኘቱ፣ እንዲሁም አንዳንድ አገሮች ባለሀብቶችን ለመሳብ መሬት በነጻ የሚሰጡ በመሆኑ በኢትዮጵያ የእርሻ መሬቶችን ለውጭ ባለሀብቶች በርካሽ ዋጋ መሸጡ ተገቢ ነው ሰሉ የመንግስታቸውን አቋም አጠናክረዋል። ወ/ሮ ገነት ይህን ይበሉ እንጅ ...

Read More »

ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች፡ “የኢትዮጵያ ፍርድ ሂደት ቀልድ ነበር” አሉ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ቆይተው የተለቀቁት የስዊዲን ጋዜጠኞች የታሰሩበት እስር ቤት በእስረኛ ብዛት ከ200 በመቶ በላይ የተጨናነቀና በሽታ የበዛበት መሆኑን ጋዜጠኞቹ አስታወቁ:: በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩበት እስር ቤት ከ200 በመቶ በላይ መያዝ ከሚችለው በላይ የተጨናነቀና ፍጽም ቆሻሳ መሆኑ ተገለጸ:: በእስር ቤቶቹ አይጦችና ዝንቦች ለታሳሪዎች መከራ መሆናቸውንም ቢቢሲ ጋዜጠኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል:: በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከመሀይምነት ባልተላቀቁ ሰዎች ብዛት ከዓለማችን ሶስተኛ ናት ተባለ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፤ ከመሀይምነት የተላቀቁ ሰዎች ብዛትን በተመለከተ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኢትዮጵያ ከዓለማችን በርካታ አገራት ከመጨረሻ ሶስተኛ መሆኗን ይፋ አደረገ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከሶስተኛ አለም አገራት ውስጥ አጥንቶ ይፋ ባደረገው በዚህ ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ፤ 28 በመቶው ብቻ ፊደል የቆጠሩና መጻፍና ማንበብ የሚችሉ ናቸው ...

Read More »

በመንግስት አና በ ኦብነግ መካከል የተጀመረው ድርድር ሳይሳካ ቀረ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለድርድሩ መደናቀፍ አንድኛቸው ሌለኛቸውን ተጠያቂ እያደረጉ ነው። በኢትዮጵያ መንግስትና በኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር መካከል የተጀመረው ድርድር አለመሳካቱን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ። ናይሮቢ ሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ድርድሩ የከሸፈው ኦብነግ የ ኢትዮጵያን ህገ-መንግስት ባለመቀበሉ ነው ሲል፤ኦብነግ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ አላስፈላጊ ቅደመ-ሁኔታዎችን በማስቀመጥ በድርድሩ ላይ እንቅፋት የፈጠረው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን ገልጿል። በጀነራል መሀመድ ኡስማን ...

Read More »

ከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነ አቶ ከሚል ሸምሱን የእግድ ይሰጥልን ጥያቄ ውድቅ አደረገው

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ካሚል ሸምሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ኡላማዎችን ምክር ቤትን በደንቡ ያልተሾሙና መርጫ ለማስተባባር ስልጣን የሌላቸው ናቸው በማለት ምክር ቤቱ እንዲታገድና እንዲበተንና ምርጫ እንዳይደረግ ይወሰንልን በማለት መክሰሳቸው ይታወሳል። ዳኛ አምባቸው ታረቀኝ መስከረም 23 ቀን 2005 ዓም በሰጡት ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ  በሀይማኖት ጉዳይ ...

Read More »

በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ። ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ  በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ...

Read More »

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ ባደረጉት ሰልፍ የኖርዌይ መንግስት በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚታወቀውን የኢህአዴግ መንግስት መደገፉን እንዲያቆምና በኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ላይ ያለውን አቋም ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሀፊ የሆኑት አቶ ቢኒያም ካሳ ለኢሳት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብቶች ጥሰቱ የሚታወቅ ቢሆንም የኖርዌይ መንግስት ግን አሁንም እርዳታውን ቀጥሎአል የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ...

Read More »