በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች።

ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።

ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ  በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው።

ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ነው።

ጓደኛዋም ከጋብቻ ውጪ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ወንጀል ተከሶ በ እስር እንደሚገኝ< አመልክቷል።

የ አንድ ቀን አራሷ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ሁለት እግሮቿ በሰንሰለት በመታሰራቸው፤ ህፃን ልጇን ሜሪያምን ማቀፍ ተስኗት መታየቷን ድረ-ገጹ አስነብቧል።

ኢትዮጵያዊቷ እናት ለፍርድ ቤት በሰጠችው ቃልም ከእስር ከተለቀቀች ከህፃኗ ጋር ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ተናግሯለች።

የወህኒዎቹ ሃላፊዎች ግን አራሷ ኢትዮጵያዊት ከወህኒ የምትወጣው የ እስር ጊዜዋን ከጨረሰች በሁዋላ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ህፃን ልጇን ይዛ መሄድ ትችላለች?ወይስ አትችልም? የሚለው ጉዳይም ለወደፊት በ ህግ የሚታይ መሆኑን ነው የገለፁት።

ወደ መካከለኛው ምስራቅና አረብ አገራት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ደረጃ በደረሰበት ሰ ዓት የ ኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመታደግ ምንም እንቅስቃሴ ሲያደርግ አመታዬቱ፤ ብዙዎችን ካሳዘነ ውሎ አድሯል።