በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ ባደረጉት ሰልፍ የኖርዌይ መንግስት በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚታወቀውን የኢህአዴግ መንግስት መደገፉን እንዲያቆምና በኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ላይ ያለውን አቋም ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሀፊ የሆኑት አቶ ቢኒያም ካሳ ለኢሳት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብቶች ጥሰቱ የሚታወቅ ቢሆንም የኖርዌይ መንግስት ግን አሁንም እርዳታውን ቀጥሎአል

የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የነበረው እቅድ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እስካሁን አለመሳካቱንም አቶ ቢኒያም ገልጿል

በሰልፉ ላይ የተሳተፉ አንዲት ኢትዮጵያዊት በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ሁለተኛ ዜጋ ሆነው መኖር ስለማይፈልጉ ወደ አገራቸው ለመመለስ አይፈልጉም

ሂውማን ራይትስን ጨማሮ በርካታ አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች የኖርዌይ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በመተቸች መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ኖርዌይ ከ400 ያላነሱ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ መዘጋጀቱዋን ማስታወቁዋ ይታወሳል።