(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ10 /2010) የአማራ ክልል ልዑክ በአስመራ ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ /አዲሃን/ ጋር ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡ አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት ልኡካን የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡበት ጉዳይ ላይ እየመከሩ መሆኑም ታውቋል በቅርቡ የአዴኃን አመራሮች በሰላም ለመታገል በመወሰናቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና ከአማራ ክልል ገዱ አንዳርጋቸው ጋር መምከራቸው ይታወሳል። በዚሁም አዲሃን ወደ ሀገሩ ገብቶ ...
Read More »ሒዩማን ራይት ዎች የለውጥ ሒደት ላይ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 10/2010)በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በተጀመረው የለውጥ ሒደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን ሒዩማን ራይት ዎች ገለጸ። ሒዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው በኢትዮጵያ በብሔርና በሃይማኖት ሰበብ የሚካሄዱ ግድያዎች ከፍተኛ ውጥረት በመፍጠር ላይ ናቸው። በተለይም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች በለውጡ ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ብሏል ሒዩማን ራይትስ ዎች። ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግስት ለውጡን የሚያደናቅፉ ግጭቶችን እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ...
Read More »የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ስጋት ውስጥ ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 10/2010) በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ለቀናት የዘለቀው አለመረጋጋት ጋብ ቢልም ነዋሪዎች አሁንም በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገለጹ። በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ ያሉት ነዋሪዎች ምግብ ባለማግኘታቸው ለረሃብ መጋለጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል። አራት ሰዎች የተገደሉበት የቴፒው ጥቃት የበርካታ ነዋሪዎች መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ማውደሙንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ዛሬ ለቴፒ ነዋሪዎች አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ በመጠየቅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደጃፍ ላይ ሰልፍ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።
Read More »በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጀመሪያው ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ የመግባባትና እርቀ ስላም ጉባኤ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጀመሪያው ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ የመግባባትና እርቀ ስላም ጉባኤ የምክክር መድረክ ተካሄደ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ በራስ ሆቴል በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ በሀገር ውስጥ ያሉ እና ከውጭ ሀገራት የገቡ 50 ፓርቲዎች ተሳትፈዋል። የጉባኤው ሰነድ ዝግጅት አስተባባሪ ንኡስ ኮሚቴ እና የሀገር ውሰጥ የብሄራዊ እርቅና ሰላም ጉባኤ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ግርማ በቀለ በተለይ ...
Read More »ከኦሮሚያ ክልል፣ ቡሌሆራ አካበቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያ የሚኖሩ የቡርጂ ብሔረሰብ አባላት ይትቃወሞ ስለፈ አድርጉ።
ከኦሮሚያ ክልል፣ ቡሌሆራ አካበቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያ የሚኖሩ የቡርጂ ብሔረሰብ አባላት ይትቃወሞ ስለፈ አድርጉ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢሳት ወኪሎች ከስፍራው ያደረሱን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተፈናቃዮቹ በዋነኝነት ሰልፍ የወጡት በመንግስት በኩል ተዘንግተናል በማለት ነው። ከነቤተሰባችን ችግር ላይ በወደቅንበት ሁኔታ አያለን መንግስት ትኩረት ሊሰጠን ይገባል ያሉት ሰልፈኞቹ ፤በግጭት ምክንያት ከአንድ አመት በላይ የተዘጋው የቡርጂ-ዲላ እና የቡርጂ-ሀገረማርያም መንገድ ...
Read More »በህገወጥ ድርጊት ቻግኒ ላይ ታስሮ የነበረ የጭነት መኪና ትናንት ነሀሴ 8 ቀን ለነሀሴ 9 ሌሊት ላይ ምሽትን ተገን አድርጎ አምልጦ ሲሄድ ከኮሶ በር ከተማ መግቢያ ከሚገኝ መንደር ውስጥ መንገድ ስቶ ከግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመግባት የአንድ ሰው ህይወት ሲያጠፋ አንድ ቤት አውድማል፡፡
በህገወጥ ድርጊት ቻግኒ ላይ ታስሮ የነበረ የጭነት መኪና ትናንት ነሀሴ 8 ቀን ለነሀሴ 9 ሌሊት ላይ ምሽትን ተገን አድርጎ አምልጦ ሲሄድ ከኮሶ በር ከተማ መግቢያ ከሚገኝ መንደር ውስጥ መንገድ ስቶ ከግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመግባት የአንድ ሰው ህይወት ሲያጠፋ አንድ ቤት አውድማል፡፡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) መረጃዎችረ እንደሚያሳዩት፣ ተሽከርካሪው ከሁለት ቀናት በፊት በአሶሳው የሕዝብ ጭፍጨፋ እጁ ...
Read More »በደቡብ ወሎ በሙስሊሞች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ አንድነት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ስራ ላይ እንቅፋት ስለሚፈጥር፣ ሁሉም አካላት ሊጠነቀቁ ይገባል ተባለ።
በደቡብ ወሎ በሙስሊሞች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ አንድነት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ስራ ላይ እንቅፋት ስለሚፈጥር፣ ሁሉም አካላት ሊጠነቀቁ ይገባል ተባለ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ አንድነት የጋራ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰሞኑን በኮምቦልቻ፣ በደሴና በከሚሴ በሙስሊሞች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል፤በርካታ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክቱዋል። በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና ...
Read More »በአሜሪካ-ሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው::
በአሜሪካ-ሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው:: ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የ10 ሺህ ሃይቆች ባለቤት ተብላ በምትታወቀው የአሜሪካዋ ግዛት ሚኒሶታ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ሊከበር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መኾኑን የፌስቲቫሉ አስተባባሪዎች በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሚኒሶታ በተጓዙበት ወቅት በተሰናዳው ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያውያኑ መከከል መለስተኛ ውጥረት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። ከዚያም ...
Read More »የሊቢያ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት 45 ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ውሳኔ አሳለፈ።
የሊቢያ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት 45 ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ውሳኔ አሳለፈ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የሀገሪቱን የፍትህ ሚኒስቴ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ፖሊሶቹ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ገድለዋል ተብለው በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው። ፖሊሶቹ ሰልፈኞች ላይ ተኩሰው ብበርካቶችን የገደሉት፣ የኮሎኔል መአመድ ጋዳፊን አገዛዝ ለማስወገድ አብዮቱ በተቀጣጠለበት ወቅት አማጽያኑ ወደ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር መሬት መስጠት አቆመ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) የአዲስ አበባ መስተዳድር መሬት መስጠት ማቆሙን በይፋ አስታወቀ። የተጀመሩ ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ከኮንዲሚኒየምና መሰል የቤት ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣም መስተዳድሩ ግልጽ አድርጓል። በኢንደስትሪ ግንባታ ጭምር የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው በተገለጸበት በዚህ መመሪያ ከበቂ ቅድመ ዝግጅት በኋላ ጉዳዮቹን መልሶ ማየት እንደሚቻልም ተመልቷል። ከግል የኢንደስትሪ አልሚዎች ጥያቄ በተጨማሪ የሰነድ አልባና አግባብ ባለው እክል ሳይፈቀዱ የተያዙ ቦታዎችን በተመለከተም የከተማው ...
Read More »