በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጀመሪያው ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ የመግባባትና እርቀ ስላም ጉባኤ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጀመሪያው ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ የመግባባትና እርቀ ስላም ጉባኤ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ በራስ ሆቴል በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ በሀገር ውስጥ ያሉ እና ከውጭ ሀገራት የገቡ 50 ፓርቲዎች ተሳትፈዋል።
የጉባኤው ሰነድ ዝግጅት አስተባባሪ ንኡስ ኮሚቴ እና የሀገር ውሰጥ የብሄራዊ እርቅና ሰላም ጉባኤ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ግርማ በቀለ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ዛሬ ውይይት የተካሄደው በቅርቡ በሲያትል ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ከተወያዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰድስቱ ፣እንዲሁም በሀገር ውሰጥ ሲታግሉ ከቆዩት አምስቱ የተካተቱበት የምክክር ኮሚቴ ወደፊት ለሚዘጋጀወረ ለበሔራዊ እርቀ ጉባኤው ባዘጋጀው መነሻ ሰነድ ላይ ነው።
የዛሬው መድረክ ለተከታዩ ትልቅ የእርቅ ጉባኤ አስፈላጊ የሆኑ ጠቃሚ ግብአቶች እንደተገኙበትም አቶ ግርማ አብራርተዋል። በዛሬው መድረክ ከውጭ ሀገራት ከገቡት ውስጥ በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የነጻ ኦሮሚያ አንድነት ግንባር ፣አቶ ሀይሉ ጎንፋ፣የ ኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር-አዴግ፣የትግራይ ዲሞክራቲክ ግንባር-ትዴግ እና የአፋር ህዝብ ፓርቲ ፣ከሀገር ውስጥ ደግሞ አረንጉዋዴ ኮከብ ፓርቲ እንዲሁም ከገዥው ፓርቲ መካከል ብአዴን መገኘቱን ከአቶ ግርማ ገለጻ ለመረዳት ተችሎአል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የመብት ድርጅቶች ህብረት ምስረታ በዓል በደሳለኝ ሆቴል መካሄዱን ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን ዘግባለች።
መስራች ድርጅቶቹ፣ሂውማን ራይት ካውንስል ፣ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ፣አድቮኬትስ ኢትዮጵያ፣ዴቨሎፕመንታል ጀስቲስ ናሽናል አሶሴሽን እና ሳራ ጀስቲስ ፍሮም ኦል ውማን አሶሴሽን ናቸው።
ህብረቱ የሚያተኩርባቸው እንቅስቃሴዎችም በስሩ ያሉ በሰብዓዊ እና ዲሞክራሲ መብቶች ላይ የሚሰሩ ማህበራትን ማስተባበር፣ማህበራቱ የጋራ መድረክ እንዲኖራቸው ማስቻል፣በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ስራዎች ላይ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ማስተባበር እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ናቸው ተብሎአል።
ማንኛውም የበጎ አድራጎት ፈቃድ ያላቸው፤ እንዲሁም ብሰብአዊ እና የዲሞክራሲያዊ መብቶች እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚሰሩ ማንኛውም ማህበራት አባል መሆን እንደሚችሉም