በደቡብ ወሎ በሙስሊሞች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ አንድነት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ስራ ላይ እንቅፋት ስለሚፈጥር፣ ሁሉም አካላት ሊጠነቀቁ ይገባል ተባለ።

በደቡብ ወሎ በሙስሊሞች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ አንድነት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ስራ ላይ እንቅፋት ስለሚፈጥር፣ ሁሉም አካላት ሊጠነቀቁ ይገባል ተባለ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ አንድነት የጋራ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰሞኑን በኮምቦልቻ፣ በደሴና በከሚሴ በሙስሊሞች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል፤በርካታ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክቱዋል።
በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና ያካል መጉደል በጥልቅ ማዘኑን የገለጸው ኮሚቴው፤ ባካባቢው ከትንንሽ ልዩነቶች ተነስቶ ወደ ግጭት የሚያመሩ ያልተገቡ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸውን አመልክቶዋል።
ይህ ተደጋግሞ የሚስተዋል ክስተት አዲሱ ኮሚቴ የጀመረውን ስራ የሚያደናቅፍና የሚያጓትት በመሆኑ የተለየ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል ኮሚቴው ሁሉንም በግጭቱ የተሳተፉ አካላትን አሰጠንቅቆአል።