የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ስጋት ውስጥ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 10/2010) በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ለቀናት የዘለቀው አለመረጋጋት ጋብ ቢልም ነዋሪዎች አሁንም በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገለጹ።

በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ ያሉት ነዋሪዎች ምግብ ባለማግኘታቸው ለረሃብ መጋለጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል።

አራት ሰዎች የተገደሉበት የቴፒው ጥቃት የበርካታ ነዋሪዎች መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ማውደሙንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ዛሬ ለቴፒ ነዋሪዎች አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ በመጠየቅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደጃፍ ላይ ሰልፍ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።