በህገወጥ ድርጊት ቻግኒ ላይ ታስሮ የነበረ የጭነት መኪና ትናንት ነሀሴ 8 ቀን ለነሀሴ 9 ሌሊት ላይ ምሽትን ተገን አድርጎ አምልጦ ሲሄድ ከኮሶ በር ከተማ መግቢያ ከሚገኝ መንደር ውስጥ መንገድ ስቶ ከግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመግባት የአንድ ሰው ህይወት ሲያጠፋ አንድ ቤት አውድማል፡፡

በህገወጥ ድርጊት ቻግኒ ላይ ታስሮ የነበረ የጭነት መኪና ትናንት ነሀሴ 8 ቀን ለነሀሴ 9 ሌሊት ላይ ምሽትን ተገን አድርጎ አምልጦ ሲሄድ ከኮሶ በር ከተማ መግቢያ ከሚገኝ መንደር ውስጥ መንገድ ስቶ ከግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመግባት የአንድ ሰው ህይወት ሲያጠፋ አንድ ቤት አውድማል፡፡
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) መረጃዎችረ እንደሚያሳዩት፣ ተሽከርካሪው ከሁለት ቀናት በፊት በአሶሳው የሕዝብ ጭፍጨፋ እጁ እንዳለበት የሚጠርጥርን አንድ የህወሀት ሹምን እና የጦር መሳሪያ በመጫን ከአሶሳ ከተማ ለመውጣት ሲሞክር ተይዞ ቻግኒ ላይ በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።
የተሽከርካሪው ባለቤት የቲሊሊ ከተማ ነዋሪ በመሆኑም መኪናው የያዘውን ህገ ወጥ እቃ እና የተለያዩ ንብረቶችን ቲሊሊ ላይ ለፖሊስ እንዲያስረክብ ተደርጎ እና በጉዳዩ ላይ ቲሊሊ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እንዲደረግበት ትእዛዝ ተስጥቶ እንዲለቀቅ ተደረገ።
ይሁንና ሾፌሩ የተሰጠውን ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተው እና ቲሊሊ ከተማ የገባ በማስመሰል በለሊት በመውጣት ወደ መቀሌ ሲጉዋዝ ኮሶ በር ላይ መንገድ ስቶ የግለሰብ መኖሪያን ደርምሶ በመግባት ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውድም ምክንያት ሆኑዋል።