የሊቢያ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት 45 ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ውሳኔ አሳለፈ።

የሊቢያ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት 45 ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ውሳኔ አሳለፈ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የሀገሪቱን የፍትህ ሚኒስቴ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ፖሊሶቹ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ገድለዋል ተብለው በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።
ፖሊሶቹ ሰልፈኞች ላይ ተኩሰው ብበርካቶችን የገደሉት፣ የኮሎኔል መአመድ ጋዳፊን አገዛዝ ለማስወገድ አብዮቱ በተቀጣጠለበት ወቅት አማጽያኑ ወደ መዲናዋ ትሪፖሊ በሚጠጉበት ወቅት ነው ተብሏል።.
የጋዳፊ አገዛዝ ከተወገደ ወዲህ በበርካታ ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ሲተላለፍ ይህ ከፍተኛ ቁጥር እንደሆነ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ አትቷል።.
ጋዳፊ ከተወገዱ ካለፉት ሰባት ዓመት ወዲህ ሰላም የራቃት ሊቢያ ወደ ቀድሞ መረጋጋቷ ለመመለስ ለዓመታት ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች።
በአንድ መዝገብ ተከሰው የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው 45 ፖሊሶች በተጨማሪ ሌሎች 54 ፖሊሶች እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት እስራት የተበየነባቸው ሲሆን፤ 22 ፖሊሶች ደግሞ በነጻ ተለቀዋል።
ይሁንና ፖሊሶቹ መቼ እንደተከሰሱ፣መቼ እንደታሰሩ እና እንዴት እንደተፈረደባቸው እስካሁን በግልጽ አለመታወቁን ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።