በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች በብዛት እየለቀቁ ነው

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በውጭ አገር አሰሪዎችና ተባባሪ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ተቆጣጣሪዎች በሚፈጸም በደል ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ገልጸዋል። በመጀመሪያዎቹ የግንባታ ወራት አገራዊ ስሜቱ ፈንቅሎት ወደ አካባቢው በመሄድ ከአንድ አመት ከስድስት ወራት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ወጣት ፣  ሰራተኛው በየጊዜው  በሚደርስበት በደል በቀን ውስጥ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ሰራተኞች ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ፦ኢትዮጵያ ኑክሌርን ጥቅም ላይ ለማዋል ቁርጠኛ ናት አሉ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-<<ኢትዮጵያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን  ሰላማዊ የልማት አጀንዳዋን ለማሳካት ብቻ ጥቅም ላይ ለማዋል ቁርጠኛ ናት>>ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። መንግስታዊው  የኢትዮጵያ  ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃለማሪያም  ይህን ያሉት፤የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩኪያ አማኖን ሰሞኑን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። <<ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ በመጠቀም ረገድ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ጋር ምንጊዜም ...

Read More »

የጸጥታው ምክር ቤት በአወዛጋቢዋ የአቢይ ግዛት ጦሩን ለማቆየት ወሰነ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሜንና ደቡብ ሱዳንን በማወዛገብ ላይ ባለችው የአቤይ ግዛት ላይ የሰፈረው 4 ሺ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ጦር ለተጨማሪ ስድስት ወራት ባለበት እንዲቆይ አርብ ውሳኔ አሳልፎአል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የሆኑት ባንኪ ሙን በአወዛጋቢዋ አቤይ ግዛት አንጻራዊ ሰላም ቢታይም ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቂ ትኩረት አለመስጠታቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቤይ የተመድን ጦር ...

Read More »

በደራ ወረዳ በተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ ፍርድ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ይላሉ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ አርሶአደርና ባለቤታቸው ላይ የተፈጸመውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፋ ካደረገ በሁዋላ ኢትዮጵያውያንን ከያቅጣጫው እያስቆጣ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው እንዲሁም ለኢሳት መልእክቶችን የሚተው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ በድርጊቱ ማዘን ብቻውን በቂ አለመሆኑን ገልጸው ወደ ተግባር መግባት አለብን ሲሉ አሳስበዋል። ሌላው  በዳላስ ቴክሳስ የሚኖሩ ግለሰብ ...

Read More »

የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፕሮፖጋንዳና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ የሆነው ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ ታሰረ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአረና የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ ወጣቱ የታሰረው በተከራየው ግቢ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው የህወሓት አባል “በግቢያችን ፖለቲካ እየሰበክ ሌሎች ሰዎችን ወደ ዓረና ትግራይ ልትወስድ ነው በማለት ባነሱት ኣታካራ ” ነው። ያለ ምንም መጥሪያና በቅርብ ይጠባበቁ የነበሩ ፖሊሶች ይዘዋቸው በመሄድ ዓዲ ሀቂ ፖሊስ ጣብያ በተባለ እስር ቤት አስረዋቸውል ይላል መግለጫው። የዓረና ትግራይ  የፅሕፈት ቤት ዶኩሜንትና ...

Read More »

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተገቢውን ዕውቅና እየሰጡ አይደለም ተባለ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ  ከዚህ ዓለም በሞት ከተሰናበቱ ወዲህ ሕዝቡ ሐዘኑን ከመግለጹ ጋር ተያይዞ “የመለስን ራዕይ ሳይበረዝ፣ሳይከለስ እናስፈጽማለን” ወደሚል ቅዥት ውስጥ መገባቱን የሚያስታውሱት ዘጋቢያችን የናጋገራቸው ባለሙያዎች ይህንን አጀንዳም እንደ ኢትዮጽያ ቴሌቪዥን ያሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ክፉኛ እያራገቡት፣በአንጻሩ ደግሞ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር መኖራቸው እንኳን እየተረሳ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ “የኢትዮጵያን ህዳሴ እናበስራለን” የሚለው ኢቲቪ በአሁን ሰዓት ...

Read More »

የሺ ጋብቻ ቅዳሜ ይከናወናል

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኤሚነንስ ሶሻል ኢንተርፐርነርስ በኢትዮጽያ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ፤መመዝገቡ የማይቀር ነው ያለውን የአንድ ሺ ጥንዶች ጋብቻ ቅዳሜ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ጎተራ ማሳለጫ የብሄር ብሄረሰቦች መንደር ተብሎ በሚታወቀው ሜዳ ላይ እንደሚያከናውን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጽያ በዚህ ደረጃና ዓይነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥንዶች በአንድነት ሲዳሩ የመጀመሪያው ሲሆን ሥነሥርዓቱም ሁሉም ተጋቢዎች የመጡበትን አካባቢ ወይም ክልል ባህል፣አለባበስ በሚያንጸባርቅ መልኩ እንደሚካሄድ ...

Read More »

ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች የፊታችን ዕሁድ ቃሊት ወህኒቤት ድረስ ተሰባስበው በመሄድ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት ማቀዳቸውን አስታወቁ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጲያ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እስር ቤት ድረስ ሔዶ ለመጎብኘት ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች በከፍተኛ መዘጋጀታቸውን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። የፊታችን ዕሁድ ቃሊት ወህኒቤት ድረስ ተሰባስበው በመሄድ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ጥሪ መተላለፉ የተሰማ ሲሆን በጉዞው ሒደት ተንኳሽ ድርጊቶች የሚፈፅሙ ሃይሎች ሠርገው እንዳይገቡ ሁሉም ሙስሊም የጥንቃቄ ርምጃ ...

Read More »

የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ

ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀና  ማሪያም  አካባቢ  መንግስት  የሚያደርገውን  መኖሪያ  ቤቶችን  የማፍረስ ዘመቻ  አስፈፃሚ  የሆኑ  የፌድራል  ፖሊሶች  ህፃን  በናትዋ  ጀርባ  ላይ  እንዳለች  በዱላ  መተው  መግደላቸው  ተዘገበ። ከ30.000 ሺህ  በላይ   አባ ወራ  በተፈናቀለበት  የንፋስልክ  ላፍቶ  ክፍለ ከተማ ወረዳ 01  መኖሪያ  ቤቶችን  የማፍረስ  ዘመቻ   ትላንት  በናትዋ  ጀርባ  እንዳለች በፌድራል ፖሊስ  ተመታ  ከሞተችው   ህፃን  ጋር  የሞቱት  ቁጥር  አራት  ደርሰዋል። መጠለያም  ...

Read More »

በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጽያውያን ከካምፕ እንዲወጡ በመደረጋቸው ለብርድና ለሀሩር መዳረጋቸውን ገለጡ

ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት  ሬዲዮ  ያናገራቸው  በሊቢያና  በቱኒዚያ  ድንበር  ላይ  የሚገኙ  ኢትዮጽያውያኖች  እንደገለፁልን  የተባበሩት  መንግስታት  የስደተኞች  ከፍተኛ ኮምሽን  ጉዳያቸውን  የያዘ  ቢሆንም  ከፊሎቹን  በስደተኝነት  ተቀብሎ  ከፊሎቹን  ሳይቀበላቸው  በመቅረቱ  ለከፍተኛ  ችግር  ተዳርገዋል ። በሊበለያ  ከ10  እስከ  20  አመት  የኖሩ  ነገር ግን  በሊቢያ  በተነሳው  ህዝባዊ አመጽ  ወደካምፕ  እንዲገቡ  ከተገደዱት  ከነዚህ  ኢትዮጽያዊያን  መካከል  የሁለት  ልጆች  እናት  የሆነችው  ኢትዮጽያዊ  እንደገለፀችልን  ያለ ...

Read More »