ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች የፊታችን ዕሁድ ቃሊት ወህኒቤት ድረስ ተሰባስበው በመሄድ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት ማቀዳቸውን አስታወቁ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጲያ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እስር ቤት ድረስ ሔዶ ለመጎብኘት ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች በከፍተኛ መዘጋጀታቸውን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል።

የፊታችን ዕሁድ ቃሊት ወህኒቤት ድረስ ተሰባስበው በመሄድ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ጥሪ መተላለፉ የተሰማ ሲሆን በጉዞው ሒደት ተንኳሽ ድርጊቶች የሚፈፅሙ ሃይሎች ሠርገው እንዳይገቡ ሁሉም ሙስሊም የጥንቃቄ ርምጃ እንዲያደርግ ተሠምቷል።

ከተለያዩ የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች ከመሐል አዲስ አበባ ወደ ፩፭ ኪሎ ሜትር በሚርቀው ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚጓዙት ኢትዮጲአውያን ሙስሊሞች የጉዟቸው ዓላማ ለታሰሩት