የጸጥታው ምክር ቤት በአወዛጋቢዋ የአቢይ ግዛት ጦሩን ለማቆየት ወሰነ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰሜንና ደቡብ ሱዳንን በማወዛገብ ላይ ባለችው የአቤይ ግዛት ላይ የሰፈረው 4 ሺ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ጦር ለተጨማሪ ስድስት ወራት ባለበት እንዲቆይ አርብ ውሳኔ አሳልፎአል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የሆኑት ባንኪ ሙን በአወዛጋቢዋ አቤይ ግዛት አንጻራዊ ሰላም ቢታይም ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቂ ትኩረት አለመስጠታቸውን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቤይ የተመድን ጦር ይመሩ የነበሩት የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ሰው የሆኑት ሜጀር ጄኔራል ተስፋየ ወረደ በሜጀር ጄኔራል ዮሀንስ ተተክተዋል። አብዛኞቹ ወታደራዊ አዛዦች በወር ከ6ሺ እስከ 14 ሺ ዶላር እንደሚከፈላቸው ከተመድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።