ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየአመቱ ታህሳስ 29 የሚከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በመላው የኢትዮጵያ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ሲሆን በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት የበአሉን ድምቀት እንደቀነሰው ምእመናን ተናግረዋል። ዘጋቢያችን ያነጋገራት አንድ የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተክርስቲያኑዋ ከሁለት በመከፈሉዋና የቤተክርስቲያን አባቶች ችግሩን ለመፍታት ባለመቻላቸው ማዘኑዋን ገልጻለች። በበአሉ ዋዜማ በተደረገው የጸሎት ስነስርአት ላይ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑዋን እንዲጎበኝ ስትጸልይ ማደሯንም ተናግራለች። ...
Read More »ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታስረዋል ተባለ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን የብሄር ግጭት ተከትሎ ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸውን የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ታስረዋል ያላቸውን የ99 ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አብዛኞቹ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ጠቁሟል። ከታሰሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች ቢሆንም፣ የአማራና የትግራይ ተማሪዎችም ይገኙበታል። ...
Read More »ባለሀብቶች ለኢህአዴግ ጽ/ቤት ግንባታ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሊሰጡ አልቻሉም ተባለ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህም ምክንያት የግንባሩ ጽህፈት ቤት ግንባታ መስተጓጎሉን ሪፖርተር ዘግቧል። ጋዜጣው እንዳለው ከአራት ዓመት በፊት ኢሕአዴግ ሰባት ፎቅ ከፍታ ያለው ሕንፃና ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ የካድሬዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡ አራት ኪሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካባቢ ይገነባል የተባለው የኢሕአዴግ ፖለቲካ ...
Read More »ግንቦት7 በሀረር ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ህወሀት መራሹ መንግስት በሀረር በታዳጊው ላይ የወሰደውን ኢሰብአዊ ድርጊት በጽኑ አውግዟል። ዜጎች መብታቸውን በጠየቁ በጥይቅ የቆላሉ ያለው መግለጫው፣ ከእንዲህ አይነት አስከፊ ስርአት ለመላቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን የትግል ጽናት በመማር ለእውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል። ህወሀት መራሹ መንግስት ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት ...
Read More »የቻይና ጋዜጠኞች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ኢህአዴግ በሙስሊሙ ተቃውሞ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቱ ታወቀ
ታህሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከኢህአዴግ ምንጮች ለመረዳት እንደቻለው ግንባሩ በየጊዜው እያየለ የመጣውን የሙስሊሞችን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የመ-= ፍትሄ ሀሳብ በማጣቱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደወደቀ ታውቋል። የመጅሊስ አመራሮች ከተመረጡ እና መሪዎቹ ወደ እስር ቤት ከተጓዙ በሁዋላ እንቅሰቃሴው ይዳከማል የሚል እምነት ይዞ የነበረው ኢህአዴግ፣ እንቅስቃሴው በተቃራኒው እየጨመረ እና የአብዛኛውን ሙስሊም ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎታል። በግንባሩ ውስጥ ...
Read More »የባለራእይ ወጣቶች ማህበር በደህንነት ሰዎች እየተዋከብን ነው ይላሉ
ታህሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማህበሩ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆነው ወጣት አለማየሁ አበበ እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ እንደገለጹት ባለፈው ሳምንት ለኢሳት ቃለምልልስ ከሰጡ በሁዋላ፣ ከአሸባሪዎች ጋር ተገናኝታችሁዋል በሚል በደህንነት ሀይሎች እየተዋከቡ ነው። ከእነርሱ አልፎ ቤተሰቦቻቸውንም ማስፈራራትና ማሸበር መጀመራቸውን ገልጸዋል። ወጣት ብርሀኑ እንደሚለው በህጋዊነት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ማህበር የተለያዩ ስሞች እየሰጡ መወንጀልና አመራሮችንም ማዋከብ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነትን ...
Read More »የርእዮት አለሙ ይግባኝ የህግ እንቆቅልሽ እየታየበት ነው
ታህሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ሰበር ችሎት የጋዜጠኛ እና መምህርት ርእዮት አለሙ የይግባኝ ክርክር ትናንት በተናጠል ያደመተ ሲሆን፣ መዝገቡ በአለበት እንደቆመ የቅርብ ቤተሰቦች እና የህግ ባለሙያዎች ለዘጋቢያችን ተናግረዋል። ስድስት ኪሎ በሚገኘው ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጠኛው ይግባኝ ከቀረበ ጀምሮ እስካሁን 4 ጊዜ ቀጠሮ የተሰጠው ሲሆን እስካሁንም አቤቱታው መቅረብ እንደሚችል እና እንደማይችል ብይን አላገኘም። ከተለምዶ የፍርድ ቤቱ ...
Read More »የሙስሊሞችን ተቃውሞ ተከትሎ የጸጥታ ሀይሎች አስከፊ እርምጃ ወሰዱ
ታህሳስ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጁምዓን ጸሎት ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መንግስት እየሄደበት ያለውን አካሄድ በመተቸት ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ በሀረር ግጭቱ ተባብሶ አንድ ከ10 እስከ 12 ዓመት የሚገመት እድሜ ያለው ኪያ የሚባል ወጣት ተገድሏል። ሀረር የሚገኙ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሙስሊሞች በ4ኛ መስጊድ ተገኝተው ስግደታቸውን ካደረሱ በሁዋላ በሰላም ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተወሰኑ ወጣቶችን ...
Read More »አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁንም በልዩ ጥበቃ ስር ነው
ታህሳስ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጸው ከትናንት ማታ ጀምሮ የደህንነት ሀይሎች በኢህአዴግ ደጋፊ ተማሪዎች እየተመሩ ለግጭቱ መነሳት እና መባባስ ምክንያት ሆነዋል ያሉዋቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ያወጡ ሲሆን፣ የተወሰኑ ተማሪዎች በግዳጅ መታወቂያቸውን ተነጥቀው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። በሳይንስ ፋኩልቲ፣ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ እና 6 ኪሎ ግቢዎች በርካታ ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሀይሎች እና ፖሊሶች እየተንቀሳቀሱ ነው። የፌደራል ፖሊስ አባላትም ...
Read More »