አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁንም በልዩ ጥበቃ ስር ነው

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጸው ከትናንት ማታ ጀምሮ የደህንነት ሀይሎች በኢህአዴግ ደጋፊ ተማሪዎች እየተመሩ ለግጭቱ መነሳት እና መባባስ ምክንያት ሆነዋል ያሉዋቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ያወጡ ሲሆን፣ የተወሰኑ ተማሪዎች በግዳጅ መታወቂያቸውን ተነጥቀው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።

በሳይንስ ፋኩልቲ፣ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ እና 6 ኪሎ ግቢዎች በርካታ ሲቪል የለበሱ የደህንነት  ሀይሎች እና ፖሊሶች እየተንቀሳቀሱ ነው። የፌደራል ፖሊስ አባላትም በቅርብ ርቀት ሰፍረው ግቢዎችን በመጠበቅ ላይ ናቸው።